ለክቡር ዶክተር አብይ አህመድ የአትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ክቡር ሆይ ትላንት፣ ግንቦት 28 ቀን 2010 አም የኢህአዴግ ስራ ስፈጻሚ ኮሜቴ በቁልፍ የአኮኖሚ ተግባር የተሰማሩና እስካሁን በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ አገልግሎት ሰጪና አምራች ድርጅቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለግል ባለሀብቶች እንዲሸጡ መወሰኑን ተረድቻለሁ፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የባቡር አገልግሎት ለሽያጭ እንዲቀርቡ መወሰኑ ከፍተኛ ሀዘንና [...]
