| Ethiopian Millenium - a satirical essay in Amharic by Mitiku Addisu |
|
|
| Written by Mitiku Addisu (adisum1@yahoo.com) | |
| Friday, 10 August 2007 | |
|
የሚሌኒየም እንቁጣጣሽና ተስፋ የምናደርገው
የሚሌኒየም ዝግጅት በአንድ መልኩ መልካምና የሚደገፍ ቢሆንም በሌላ መልኩ የተዛነፈ ጐን ይታይበታል። መጀመሪያ ስም አጠራሩን እንመልከት። ቃሉ በአማርኛ ተመጣጣኝ ፍቺ ሳይገኝለት በጥድፊያ መሃላችን ገብቶ በቋንቋና በባህል ለያይቶናል። የልማትና የአስተዳደር ታሪካችንም እንደዚሁ ከዚህ ከግርግር ባህል ለመላቀቅ አለመቻሉ ሊያሳስበን ይገባል። አንዴ ዘመቻ፣ አንዴ አዋጅ፣ አንዴ ግምገማ፤ ይኸ ፖሊሲ፣ ያ ፖሊሲ እያልን ኖረናል። ባጭሩ፣ ያልተዘጋጀ አእምሮ ለኋላ ቀርነት የማያቋርጥ አሣር ነው ቢባል የተጋነነ አይሆንም። |
| < Prev | Next > |
|---|












