WARKA Forum Index
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 
Become a supporting member
CyberEthiopia Home | About us | Contact us
ፕሮቴስታንቶች የሚያምኑትን አያውቁም ! (ተከታታይ ማስረጃ )!!
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General
 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዋሕድ

ኮትኳች

Joined: 03 Apr 2009
Posts: 256

PostPosted: Wed Nov 18, 2009 8:30 am    Post subject: Reply with quote

ደግሞ ተደጋግሞ ይነበብ !

እውነትም መናፍቃን የሚያምኑትን አያውቁም !!

ዋሕድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ብሩክ ነህ ጌታ

መንገደኛ

Joined: 04 Feb 2010
Posts: 3

PostPosted: Thu Feb 04, 2010 4:12 pm    Post subject: Reply with quote

እንኩዋን ለአቢይ ጾም አደረሳች

ይህ ርዕስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይቀጥላል ::

ብሩክ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ሀሁሁሁ

ኮትኳች

Joined: 20 Jan 2006
Posts: 252

PostPosted: Thu Feb 04, 2010 6:46 pm    Post subject: Reply with quote

ብሩክ ነህ ጌታ

የምታምነውን አውቀህ እንደመጣህ ተስፋ አደርጋለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ብሩክ ነህ ጌታ

መንገደኛ

Joined: 04 Feb 2010
Posts: 3

PostPosted: Thu Feb 04, 2010 9:04 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ ሥላሴ - አሜን ::

ፕሮቴስታንቶች (መናፍቃን ) "ሀይማኖት " ወይም "እምነት " አለን ለማለት ምን እንደሚያምኑ ማወቅ አለባቸው :: በዘፈቀደ እየኖሩ , በደመነፍስ አምነናል እያሉ ... ምንም የሀይማኖት መልክ ሳይኖራቸው , እምነታችንን ይህ ነው ... ብለው እንኳን አስረግጠው የሚናገሩት ሳይኖራቸው .. እንዴት ለሌላው ስለራሳቸው ለመናገር እንደሚችሉ እንኳን የሚገርም ነው ::

መናፍቃን ምን እንደሚያምኑ እና እንደማያምኑ አያውቁም :: መጽሀፍ ቅዱስን ይሸከሙታል እንጂ አያውቁትም . ባገኙት የሱሪ ኪስ እየሸጎጡ ቃሉን ያንገላታሉ እንጂ ..... ምንም አይነት የመጽሀፍ ቅዱስ እውቀትና ሙላት የላቸውም ::

ታዲያ - ለሌላው አዋቂ እንዴት ሊመስሉ ቻሉ ? .. ብዙዎች የማያስተውሉ ሰዎችስ " .. እነሱኮ .. መጽሀፍ ቅዱስን ጠጥተውታል .. ከነሱ ጋር ክርክር .. ቢቀር ይሻላል " ሊሉዋቸው ቻሉ ? ምን ሲያደርጉ አይተዋቸው ነው ?

በአንድ ነገር ርግጠኛ እንሁን - ፕሮቴስታንቶች ምንም አይነት የመጽሀፍ ቅዱስ እውቀት የላቸውም :: የሚገርመው እንደ ፌንጣ ከአንዱ እስ ወደሌላው . ከአንዱ ጉዳይ ወደ ሌላው መፈናጠር እንጂ , አንድም ጠልቀው ሊያስረዱ የሚችሉት የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል የለም ::

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዳዲስ ርዕሶችን እያነሳን እንመጣበታለን ::

ይቆየን ::
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ብሩክ ነህ ጌታ

መንገደኛ

Joined: 04 Feb 2010
Posts: 3

PostPosted: Sun Feb 07, 2010 11:52 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ ሥላሴ - አሜን

ለክርስቲያኖች ሁሉ እንኩዋን ለአቢይ ጾም አደረሳችሁ እላለሁ :: ያደለውና የክርስቶስ የሆነ "ሙሽራው ከነሱ በተለየ ጊዜ ይጾማሉ " ሲል ጌታችን የተናገረውን ቃል ይዞ ይጾማል :: ያላደለውና የሰይጣን የሆነ ደግሞ "ወደ ሆድ የገባ አያረክስም " እያለ ያገኘውን ይከታል ::

ቅዱስ ጳውሎስም "ሆዳቸው አምላካቸው ነው , ክብራቸው በነውራቸው ነው " ያለው ቃል እዚህ ላይ ይፈጸማል ::

መናፍቃን እምነት ስለሌላቸው , ሀይማኖት ስለሌላቸው , ምግባር ስለሌላቸው , ጾም ስለሌላቸው , ስግደት ስለሌላቸው , ምጽዋት ስለሌላቸው , ቅዱሳን ስለሌሏቸው , መላዕክት ሰለሌሏቸው , ጌታችን ስለሌላቸው , ቤተክርስቲያን , መዝሙር ... ስለሌላቸው .. ከነሱ ጋር በምን ልንነጋገር እንደምንችል ተግባቦት ላይ መድረሱ በራሱ አስቸጋሪ ነው :;

ቅዱስ መጽሀፍ "የእግዚአብሔርን ቃል ለራሳቸው እንደሚመች ያጣምማሉ " እንዳለ .... ለስጋዊ ኑሯቸው , "ስራ ስለሆነ " የማያምኑትን ጥቅስ ይጠቅሳሉ , የማይቀበሉትን መጽሀፍ ይሸከማሉ ::

ፕሮቴስታንቶች እምነት የላቸውም - ምን እንደሚያምኑም አያውቁም :: ለድርጅታቸው አባልነት የሚመለምሉዋቸውን , እንዲሁ ክርስቲያን እንዲመስሉ ብቻ "ስምንት " ጥቅሶችን ያስጠኗቸዋል :: እነዚያን ስምንት ጥቅሶች በቃል ስለሸመደዱ ብቻ ያወቁና የበቁ አርገው ራሳቸውን ይቆጥራሉ ::

ሌሎች የማያስተውሉም "መጽሀፍ ቅዱስን የጠጡ " አርገው ይገምቱዋቸዋል :: ለሚያስተውል ግን አሳፋሪዎች ሆነው ይገኛሉ ::

ስለምንም ነገር ርዕስ ከተነሳ , እነዚያ የሸመደዱዋቸው ስምንት ጥቅሶች እንደምንም ይጠቀሳሉ :: ምንም የማይገናኝ ዕስም ቢሆን የሚጠቀሱት እነሱ ናቸው :: [ቢያንስ 95% የሚሆኑት ፕሮቴስታንቶች በሽምደዳ የሚያውቁዋቸው ጥቅሶችን .. ከዚህ በፊት ስለጻፍኩዋቸው ወደሁዋላ ሄዳችሁ ተመልከቱ ]

አንድ ጊዜ አንድ መናፍቅ ሁለት ልጆችን አስቁሞ .. እንደተለመደው እጆቹን እያወናጨፈ , የያዘውን መጽሀፍ ቅዱስ እንዳልባሌ እያወዛወዘ .. የተለመዱትን "ደመና " "በረከት " "ፈውስ " " "ልሳን ".... ቃላት እየደጋገመ እንደመወራጨት እያደረገው ሲናገር . ለመስማት ጠጋ አልኩ ::

እንዲህ አለ ".. እና አየህ ጌታ በማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት ላይ አማላጃች እኔ ነኝ እንጂ ሌላ ማንም የለም ብሏል ..." አለ ::

እነዚያ የዋሀን አቀርቅረው ይሰማሉ :: ማቲዎስ ወንጌል 4 ላይ የት ቦታ እንደዚያ እንደሚል በርጋታ ጠየኩት :: "እንዴት ይህን አታውቅም .. ቤት ስትደርስ አንብበው .." አይነት ነገር መለሰልኝ :: እኔ ግን በዚያ ዕራፍ እሱ የሚለው ነገር እንደሌለ አውቅ ነበር :: ለጊዜው ልጆቹን አስጥዬ ዕራፉን በሙሉ አነበብኩላቸው , የተጻፈው ሌላ , እሱ የሚለው ሌላ ....

እንደዚህ አይነት ማታለል ስንቱ ተሸውዶ ይሆን ? .. አንዳንዶቻችንስ የኛን አለማወቅ ለመሸፈን .. እነሱን አዋቂ የምናደርጋቸው ለምንድነው ? .. ምንም የሚያምኑትን ሳያውቁ በደመነፍስና በማታለል እየመጡ ስንቶቹን ወደ እሳት ወስደዋል ?

መጽሀፉ እንዲህ ይላል "የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ .." :: አንታለል :: ፕሮቴስታንቶች የሚያምኑትን አያውቁም :: እኛ ምንም ባናውቅ - እነሱን አዋቂ በማሰኘት የኛን አለማውቅ መሸፈን አንችልም ::

እኛ ምንም አንወቅ , አንድ ጥቅስም በቃላችን አንያዝ , ቀላሉም ነገር ከባድ ይምሰለን ..... ምንም አይነት የመጽሀፍ ቅዱስ እውቀት አይኑረን .. ባንድ ነገር ግን ርግጠኛ እንሁን - ፕሮቴስታንቶች የሚያምኑትን አያውቁም - እምነትም የላቸውም :: ከነሱ የሀሰት ዕውቀት የኛ ምንም አለማወቅ ይሻላል ::

ይቀጥላል ::
ወስብሀት እግዚአብሔር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

መስቀሉ

ዋና ኮትኳች

Joined: 24 Sep 2005
Posts: 526
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 2:55 am    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን
የተከበራችሁ ወገኖች በዚህ አምድ መነሻ የሚያምኑትን ያማያውቁ እምነታቸውን እንደ ርስት ከእናት ከአባት በመቀበል መጽሀፍ ቅዱስ ምን ይክላል እምነቴ በመጽሀፍ ቅዱስ መሰረት ነው ወይ የማይሉ ናቸው ::
በዚህ ጉዳይ ዝም ብሎ በመነዳት በሀይማኖት ትምክህት የተሞላው የተዋህዶው ማህበረሰብ ኦርቶዶክስ የሚለውን ርቱእ የእምነት መጠሪያ መያዙ ተገቢ አይደለም ::መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚል አይሁድ ከአብርሀም ዘር በመወለዳቸው ብቻ የአዲሱ እስራኤል ዘር አልሆኑም ይልቁንስ መሲሁን ክርስቶስን ስላልተቀበሉ ወገን መሆናቸው ቀርቷል ::ነገር ግን በስሙ በክርስቶስ ላመኑ የእግዚአብሄር ልጅነት መብት ተስጥቷል :;ዮሀንስ 1:12
መስቀሉ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ዘእግዚነ

ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 257

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 4:26 am    Post subject: Reply with quote

መስቀሉ :
አንተ ለመሆኑ የምታምነውን ታውቀዋልህ ? ዋርካ ውስጥ ከገባሁ ጀምሮ አንድም አምድ የእምነት ነገር ወይም ደግሞ የሚያስተምር ወይም ፍሬ ያለው ነገር ስትጽፍ አላየሁህም :: የምትመጣ ለአንድ ነገር ብቻ ነው :: ያም ተዋህዶንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለመሳደብ :: ምኑ ነው ያደረብህ ወዳጀ ?

ክርስቶስ አይንህን ያብራልህ

መስቀሉ እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን
የተከበራችሁ ወገኖች በዚህ አምድ መነሻ የሚያምኑትን ያማያውቁ እምነታቸውን እንደ ርስት ከእናት ከአባት በመቀበል መጽሀፍ ቅዱስ ምን ይክላል እምነቴ በመጽሀፍ ቅዱስ መሰረት ነው ወይ የማይሉ ናቸው ::
በዚህ ጉዳይ ዝም ብሎ በመነዳት በሀይማኖት ትምክህት የተሞላው የተዋህዶው ማህበረሰብ ኦርቶዶክስ የሚለውን ርቱእ የእምነት መጠሪያ መያዙ ተገቢ አይደለም ::መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚል አይሁድ ከአብርሀም ዘር በመወለዳቸው ብቻ የአዲሱ እስራኤል ዘር አልሆኑም ይልቁንስ መሲሁን ክርስቶስን ስላልተቀበሉ ወገን መሆናቸው ቀርቷል ::ነገር ግን በስሙ በክርስቶስ ላመኑ የእግዚአብሄር ልጅነት መብት ተስጥቷል :;ዮሀንስ 1:12
መስቀሉ

_________________
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፤13
http://www.wongelforall.wordpress.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ብሩክ ነህ ጌታ

መንገደኛ

Joined: 04 Feb 2010
Posts: 3

PostPosted: Thu Feb 11, 2010 1:52 am    Post subject: Reply with quote

በስመ ሥላሴ - አሜን ::

ውድ ክርስቲያኖች :: ፕሮቴስታንቶች (መናፍቃን ) ምን እንደሚያምኑ የማያውቁ - ግራ የገባቸውና እዚህም እዚያም የሚረግጡ መሆናቸውን በብዙ ማስረጃዎች አይተናል ::

ሁለት ታክቲኮች አሏቸው ::

1 - ምንም የማያውቅ ሰው ሲያጋጥማቸው - ከስራ ሁሉ ይቀራሉ እንጂ አባብለው ወደነሱ ሳይወስዱ ንዝንዛቸውን አያቆሙም ::

2 - መጽሀፍ ቅዱስን የሚያውቅና ቃሉ የገባውና መልስ የሚሰጣቸው ካጋጠማቸው ደግሞ - የሌላቸውን ስራ አለን , የሌላቸውን ቀጠሮ አለን ብለው ሹልክ ይላሉ :: ስራቸው የጨለማ ስራ ነውና ብርሀን ፊት መቆም አይችሉም ::

ቀድሞውኑ ግን ብዙዎች አንድ መናፍቅ ላስረዳች ሲላቸው እሺ ብለው ለመስማት የሚዘጋጁት ለምንድነው ? አንዱ ምክንያት አንዳንዶች እነሱ የሚያውቁ መስለው ስለሚገምቱዋቸውና ቀድመው ራሳቸውን እውቀት ዝቅ ስለሚያደርጉ ሲሆን ያም ደግሞ በህይወታቸው ሙሉ ሲሰሙት በነበረው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ዕምሮዋቸው በመያዙ ነው ::

.. ብዙ ከመስማት የተነሳ እውነት አርገው አንዳንዶች የሚቆጥሩት :- መናፍቃን (ፕሮቴስታንቶች ) መጽሀፍ ቅዱስን ያውቃሉ , ጥሩ ሰዎች ናቸው , አይጠጡም , አያጨሱም , አያታልሉም ... ወዘተ . የሚሉትን ወሬዎች ነው ::

ቀርበን ካወቅናቸው ግን ከነዚህ አንዱም ውስጥ እንደሌሉበት እንረዳለን :: ቃሉን አንድም እንደማያውቁ , ምንም ዐይነት የመጽሀፍ ቅዱስ እውቀት እንደሌላቸው , የአንዲት ተራ ጥቅስ ትርጉም እንኩዋን ሊነግሯች እንደማይችሉ ከዚህ በፊት አይተናል ወደፊትም እንመጣበታለን ::

አይጠጡም - አያጨሱም ወዘተ . ግን .. ከማሳቁም ሌላ የአለም መጠጥ ፋብሪካዎች , የአለም የሲጋራ ኩባንያዎች .. ... ለማን ተከፈቱና ?

ከአሜሪካ ህዝብ 70 ከመቶው ፕሮቴስታንት ነው :: ልብ በሉ , ይህ ፕሮቴስታንት የሆነው ህዝብ ግን የማይጠጣው የመጠጥ አይነት , የማያጨሰው የሀሽሽ አይነት የለም :: ወንድ ለወንድ - ሴት ለሴት መጋባት ይፈቀድ ብለው በየከተማው ሰልፍ የሚወጡት እኮ ቢያንስ 90 ከመቶው ፕሮቴስታንቶች ናቸው ::

አሜሪካ ውስጥ ያሉት ለቁጥር የሚያዳግቱ የሲጋራ ፋብሪካዎች , የሀሺሽ መተላለፊያዎች , የጠንካራ ሊከር (ሀርድ ሊከር ) ኩባንያዎች .. በሙሉ እኮ ትልቁ ገበያቸው ጴንጤው ነው ::

አውሮፓ ብንሄድ የመናፍቅ (የጴንጤ ) ምንጭ የሆነችው ጀርመን (ማርቲን ሉተርን ልብ ይሏል ) .. የምትታወቀው በቢራዋ ነው :: እነ ዴንማርክና ስዊድን (ዛሬ ለአበሻ ጴንጤዎች ዋና የገንዘብ ምንጭ የሆኑት ) .. የሚታወቁት ግብረሰዶምን በህግ በመፍቀድ , ልቅና ባደባባይ የሚታይ ወሲብ ገንዘብ እየተከፈለ የሚታይባቸው , ዜጎቻቸው ምሳ በቢራና በአልኮል መጠጥ ካልሆነ ከጉሮሮዋቸው የማይወርድላቸው ጴንጤዎች ናቸው ::

እና ማነው ጴንጤዎች አይጠጡም , አያጨሱም ያለው ??

አንድ ጥያቄ እዚህ ጋር ይነሳ :: የአበሻ ጴንጤዎች ለምን አንጠጣም ይላሉ ? (እሱም ኢትዮጵያ ያሉት ብቻ ?) ... መልሱ ዕድሜ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይበሉ ነው :: ምክንያቱም እኛ ፊት ስለሚያፍሩ , ቅዱስ ጳውሎስ "እንደበሽተኛ በቃሉ መዋጋትን ይመርጣሉ " እንዳለ በቃሉ ሊዋጉን ሲመጡ እየሰከራችሁ ? እያጨሳችሁ ? እንዳንላቸው ትንሽ ለየት ያለ ጸባይ ለማሳየት አገር ቤት ያሉት ብቻ አንጠጣም ይሉ ጀምር :: እሱም በጊዜው ለፕሮፓጋንዳ ጠቅሟቸዋል ::

አሁንም ልብ እንበል አለመጠጣትና አለማጨስ የጽድቅ ምልክት አይደለም :: እስላምም አይጠጣም , ቡድሀም አይጠጣም - ምናልባት እምነት የሌለው የማያጨስና የማይጠጣም ሞልቷል ::

ምንም አዲስ ነገር የለም :: ዋናውን ጌታ ክዶ - አማላጅና የግል አዳኝ , ፍጡርና , ተራ ሰው ነው እያሉ .. አንጠጣም አናጨስም ................ ይቺ ቀልድ ናት ::

እንደግመዋለን :: የዐለም ትላላቅ የመጠጥና የሲጋራ ኩባንያዎች የተከፈቱት በጴንጤዎች ለጴንጤዎች ነው :: ከአለም ግብረሰዶማውያን ቢያንስ 90 ከመቶው ጴንጤዎች ናቸው ::

ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል ::

መናፍቃን (ፕሮቴስታንቶች ) የሚያምኑትን አያውቁም ::
ይቆየን ::
ወስብሀት እግዚአብሔር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

መስቀሉ

ዋና ኮትኳች

Joined: 24 Sep 2005
Posts: 526
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Feb 11, 2010 10:16 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን
ወገን ዘእግዚእነ እኔ መስቀሉ ያመንኩትን በደንብ አውቃለሁ ሀሳብ አይግባህ ::እኔ የማምነው ከቅድስትድንግል ማርያም ተወልዶ ለሰው ዘር ቤዛ ለመሆን መከራ ተቀብሎ በተሰቀለ በሞተና በሶስተኛው ቀን ሞትን አሸንፎ በነተሳው ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻውም ያመኑትን ልጆቹን ሊሰበስብ በሚመለስ ብቸኛው ጌታ ነው ::
ከዚህ በተረፈ ትክክለኛ ኦርቶዶክስ ርቱእ ቀጥተኛ መጽሀፍ ቅዱስና የመጽሀፍ ቅዱስን ዋና መሰረት ክርስቶስን ብቻ የሚቀበለውን የሚሰብክ አልቃወምም ::ነገር ግን ኦርቶዶክስ ሳይሆኑ ኦርቶዶክስ ነን ብለው መላክትና ጻድቃንን ለመዳን የሚጠሩና የሚዘክሩ ኦርቶዶክስ ብዬ ፈጽሞ አልቆጥርም ::
መስቀሉ

ዘእግዚነ እንደጻፈ(ች)ው:
መስቀሉ :
አንተ ለመሆኑ የምታምነውን ታውቀዋልህ ? ዋርካ ውስጥ ከገባሁ ጀምሮ አንድም አምድ የእምነት ነገር ወይም ደግሞ የሚያስተምር ወይም ፍሬ ያለው ነገር ስትጽፍ አላየሁህም :: የምትመጣ ለአንድ ነገር ብቻ ነው :: ያም ተዋህዶንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለመሳደብ :: ምኑ ነው ያደረብህ ወዳጀ ?

ክርስቶስ አይንህን ያብራልህ

መስቀሉ እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን
የተከበራችሁ ወገኖች በዚህ አምድ መነሻ የሚያምኑትን ያማያውቁ እምነታቸውን እንደ ርስት ከእናት ከአባት በመቀበል መጽሀፍ ቅዱስ ምን ይክላል እምነቴ በመጽሀፍ ቅዱስ መሰረት ነው ወይ የማይሉ ናቸው ::
በዚህ ጉዳይ ዝም ብሎ በመነዳት በሀይማኖት ትምክህት የተሞላው የተዋህዶው ማህበረሰብ ኦርቶዶክስ የሚለውን ርቱእ የእምነት መጠሪያ መያዙ ተገቢ አይደለም ::መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚል አይሁድ ከአብርሀም ዘር በመወለዳቸው ብቻ የአዲሱ እስራኤል ዘር አልሆኑም ይልቁንስ መሲሁን ክርስቶስን ስላልተቀበሉ ወገን መሆናቸው ቀርቷል ::ነገር ግን በስሙ በክርስቶስ ላመኑ የእግዚአብሄር ልጅነት መብት ተስጥቷል :;ዮሀንስ 1:12
መስቀሉ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ብሩክ ነህ ጌታ

መንገደኛ

Joined: 04 Feb 2010
Posts: 3

PostPosted: Tue Feb 16, 2010 8:45 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ ሥላሴ - አሜን ::

በክርስቶስ ደም የተዋጃች , ከሀጢአት ወደ ጽድቅ - ከጨለማ ወደ ብርሀን - ከህይወት ወደ ሞት , ከግራ ወደ ቀኝ በፍቅሩ ያሻገራች ክርስቲያኖች - በድጋሚ እንኩዋን ለጾሙ በረከት አደረሳችሁ ::

ክርስቲያኖች ሲጾሙ - ሰይጣንና አገልጋዮቹ ደግሞ ፈተናቸውን ያጠብቃሉ :: ምክንያቱም ...." እንደነሱ አይነቱ አጋንንት ከጾምና ከጸሎት በቀር አይወጣም " ተብሏልና , ጾምና ጸሎት ለመናፍቃን ራስ ምታት ናቸው ::

ለዚህም እኮ ነው - ላለመጾም ስለፈለጉ ብቻ "እኔ የምጾመው ለጌታ ነው ባደባባይ አይደለም " በማለት ያገኙትን 365 ቀን የሚበሉት :: ለዚህም ነው .. ደሞ ሀሳባቸውን ቀየር ያደርጉና ... የነሱ አለመጾምና ለሆድ መገዛት ሳያንስ የሌላው መጾም ስለሚያናድዳቸው "ወደ ሆድ የሚገባ አያረክስም " ተብሏል እያሉ ለምን ትጾማለህ ? ለማለት የሚዳዳቸው :: ... ለዚህም እኮ ነው , ደግሞ አንዳንዴ በዚህኛው አላስኬድ ሲላቸው ... "ክርስቶስ እኮ የጾመው 40 ቀን ብቻ ነው , እናንተ ለምን 55 ቀን ትጾማላች ? ሲሉ የሚደመጡት ::

በማስተዋል ስናያቸው .. ሶስቱም ክርስቲያኖችን ለማዘናጋትና ከጾምና ከጸሎት ለመለየት ሰይጣን የሚጠቀምባቸው መንገዶች ውስጣቸው ገለባ ናቸው :: የሚገርመው ጌታችንም በጾም ላይ ሳለ , ሰይጣን እንዲሁ 3 ጥያቄዎች አቅርቦ ነበር ሊፈታተነው የሞከረው , ዛሬም የሰይጣን የሆኑቱ የክርስቶስ የሆነነው እኛን እንዲሁ በሶስት ነገሮች (ከላይ በጠቅስኩዋቸው ) ሊፈታተኑን ይሞክራሉ ::

"እስከመጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል " ነውና በፈተና እየተሰነካከልን እንዳንወድቅ ከጌታችን ልንማር , ሰይጣንንም "ሂድ አንተ ሰይጣን " ልንለው ያስፈልጋል ::

ለዚህም ነው ፕሮቴስታንቶች (መናፍቃን ) ምን እንደሚያምኑ የማያውቁ , ግራ የገባቸውና እጃቸውን ለሰይጣን የሰጡ ሆነው የምናገኛቸው :: በፍጹም በአንድ ነገር ላይ አንድ ዐይነት እምነት የላቸውም :: አሁን ያሉትን አሁን ይክዳሉ , ለነሱ ትልቁ ነገር , ዋሽቶና ቀባጥሮ ክርስቲያኖችን ወደነሱ ካምፕ ማስገባት ነው ::

ስለ ጾም ሲነሳ ... መጀመሪያ የጾም ደጋፊ ለመምሰል ይሞክሩና .. ጾምማ ጥሩ ነው .. እኛም እኮ እንጾማለን .. አታውቅም እንዴ ? እንደናንተ ከጠዋት ጀምረን 13 ዐይነት የጾም በያይነቱ እየበላን አይደለም .. በማለት ስለኛ እኛ ሳይሆን እነሱው ሊናገሩልን ይሞክሩና ይኮፈሳሉ ::

ስለኛ እኛው እንናገር ግን እናንተ መቼና የት ነው የምትጾሙት ? ሲባሉ .. እኛ ከጌታ አንድ ነገር ስንፈልግ በቃ ማንም ሳያውቅ እንጾማለን .. አየህ እሱም እኮ ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ ብሏል .. በማለት የማይገናኙ ጥቅሶችን መጥቀስ ይጀምራሉ ::

እኛ እንደነሱ በማጣጣልና በማራከስ አንጀምርም :: ጥሩ ነው , እንደአፋች ያርገውና መጾማችሁ ጥሩ ነው , ግን እናንተ የምታወሩት አንድ ክርስቲያን ከአምላኩ ጋር ተነጋግሮ ለተለየ ሰጦታ ወይም ጥያቄ ሌላው ሳያውቅ ሊጾም ይችላል :: እሱ ችግር የለውም :: ነገር ግን በማህበርና በህብረት የጾም ጊዜ ወስኖ መጾም ደግሞ ያስፈልጋል :: ያንንም መጽሀፍ ቅዱስ አንድ ቦታ "ጾምን አውጁ - ጉባኤውንም ቀድሱ " ሲል ሌላ ቦታ ደግሞ የነነዌ ሰዎች በአዋጅ በህብረት መጾማቸው , ሌላ ቦታ ደግሞ "ሙሽራው ከነሱ የሚለይበት ጊዜ ይመጣል , በዚያን ወራት ይጾማሉ " ሲል ክርስቶስ መናገሩ ... ቅዱስ ጳውሎስም "የጾም ወራት ባለፈ ጊዜ .." በማለት የጾም ወር የሚባል ወቅት መኖሩን ተናግሯል - ታዲያ እንዚህ ሁሉ የህብረትና የአዋጅ ጾም ስለመኖሩ የሚናገሩ አይደሉምን ? ስንላቸው .. .... ሁሉንም ይተዉና ... የነነዌ ሰዎች የጾሙት ያን ጊዜ ችግር ስለነበረ ነው .. በማለት "አሁን ችግር በዐለም ላይ ስለሌለ ጾም አያስፈልግም " የሚል ስሜት ያለው መልስ ይሰጣሉ ::

በአንድ በኩል "እኛም እኮ እንጾማለን " ብለው የጀመሩት ጉንጭ አልፋ ክርክር .. ሳይስቡት ጾምን በመቃወም ሞቅ ይላል :; ሳያስቡት የጾም ተቃራኒ ይሆናሉ ::

ብቻም አይደለም .... የነሱ አለመጾም አንሶ .. ትንሽ ጊዜ አብሮ ለቆያቸው ሰው ..ይህን አልበላም እጾማለሁ ካላቸው .. እነሱም መልሰው "ወደ ሆድ የሚገባ አያረክስም - ዝም ብለህ ብላ " ማለት ይጀምራሉ ::

ጥቅሱ የተጠቀሰው እጅን ታጥቦ ስለመብላትና ስለ አለመብላት ቢሆንም እነሱ ጾምን ለመቃወም ይጠቅሱታል :: የዚህ ቃል ትርጉም በደንብ ሲብራራላቸው ደግሞ እንዲህ ይላሉ ....... "ባክህ ወግ አታጥብቅ . ጌታ የጾመው አርባ ቀን .. እናንተ 55 ቀን .. ለመሆኑ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ 55 ቀን ጹሙ የሚል አለ ?" በማለት ይጠይቃሉ ::

ሰይጣን ካለሆነ በቀር ለምን አርዝማች ትጾማላችሁ የሚል ሊኖር አይገባም ነበር :: እንኩዋን 55 ቀን 55 አመት ብንጾምስ ? .. ይልቁኑ 40ውን ቀን ቀንሰን 35 ብናደርገው .. ያኔ ነበር "ለምን ቀነሳች ?" የሚል ጥያቄ ቢነሳ የሚያምረው ?

በዚያም ሆነ በዚህ ግን አላማው ጾምን ማስቀረት , "ሆዳቸው አምላካቸው ነው " እንዳለ , ሆድን አምላክ ማድረግ ነው :: እኛ ለጌታ ነግረን እንጾማለን እያሉ ይናገሩ እንጂ አንድም መናፍቅ ጾም የሚባል ነገር እንደማያውቅ መናገር ይችላል :: እንዲያውም ድርጅታቸው ጾም እንጀምር ቢል ብዙዎች ጥለው ሊወጡ ሁሉ ይችላሉ ::

ጾም ከጌታ የተሰጠን ሰይጣንን ድል ከምንነሳበት መሳሪያ አንዱ ነው :: እኛ እንጾማለን - መናፍቃን - ምን እንደሚያምኑ ስለማያውቁ ... እንደ ፈለጉ ይብሉ :: እኛ አገራችን በሰማይ ነውና ከላይ የሚመጣውን እንጠብቃለን - እነሱ ሀሳባቸው ምድራዊ ነውና ለስጋቸው የሚሆነው ላይ ያተኩሩ ::

ይቆየን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ዘላለማዊ

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Aug 2004
Posts: 675
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Feb 17, 2010 3:47 pm    Post subject: ጾምና ጸሎት Reply with quote

ያገር ልጅ ብሩክነህ እንዴት ከርመሃል። ከረጅም ጊዜ በኋላ የብዕር ስምህን ስመለከት (በአማርኛ ተተርጓሟልና ሌላ ሰው ካልሆንክ ) መጣጥፍህን ለማንበብ ጎራ አልኩ። በጾምና በጽሎት ላይ ያለህን አቋም በአንድ ትንፋሽ እረፍት ሳላደርግ ወጣሁት። አንዳንዶቹ አሳቦችህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የጎደላቸው ሆነው አገኘሁዋቸውና ትንሽ የማስበውን በቅዱስ ቃሉ መሠረት ለማለት ወደድኩ።

ጾምና ጸሎት በክርስትና ትልቅ ስፍራ ያለው ነገር ነው፤ እጅግም የከበረ እና ሰው በፈጣሪ አምላክ መንፈስ ምሪትና ቁጥጥር ስር እንዲውል የማድረግ ብቃት ያለው የመንፈሳዊ ህይወት ክፍል ነው። ወደ ጾምና ጸሎት ለመግባት ግን አስቀድሞ የፈጠረንን፣ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ስለዕኛ በደል የተሰቀለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ይጠይቃል። በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተኃይማኖት አካባቢ ደግሞ የጎደለ ትልቅ እውቀት ቢኖር የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ነው። አብዛኛው አማኝ በደብሩ ያለውን ታቦት ጠንቅቆ ያውቅ ይሆናል፣ አሊያም ማርያምን ያከብር ይሆናል፤ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትና አዳኝነት ምንም እውቀት የለውም ቢባል ማጋነን አይደለም። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂዋ የኦርቶዶክስ ቤተኃይማኖት ነች። ሕዝቡን ሰብስቦ ወንጌልን ከማስተማር ይልቅ ስለዝክር፣ ስለአርባና ስለልዩ ልዩ የኃይማኖት ተረቶች ማውራት ይበልጥባታልና። በቅርቡ በሚሊንየም አዳራሽ በአዲስ አበባ የተከናወነውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮግራም ከተከታተሉ ሰዎች ለመረዳት እንደቻልኩት መልካም ጅማሬ ነው የሚያስብል ነው፤ ወንጌል ተሰብኳልና።

ወደ ጾምና ጸሎቱ ስንመጣ፤ ጌታ ኢየሱስ አስጠንቅቆ ያስተማረው ነገር ቢኖር ይህ በአደባባይ ነጋሪት የሚመታለት ድርጊት አለመሆኑን ነው። ወደ ሆድ የሚገባ አያረክስም የሚለውን ከጾም ለመሸሸ የሚጠቀም ሰው እስከዛሬ ገጥሞኝ አያውቅም። ወደ ሆድ የሚገባ አያረክስም የሚለው ከጾም ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለውም። ጾምና ጸሎት ከፈጣሪ አምላክ ጋር በጽሞና የሚገናኙበት፣ ነፍስ በፈጣሪዋ ፊት የምትዋረድበት፣ ሥጋ ለመንፈስ ቅዱስ ስፍራውን የሚለቅበት የመንፈሳዊ ህይወት ወሳኝ ተግባር ነው። ስለዚህ ወደ ሆድ የሚገባ አያረክስም በሚል ሰንካላ ምክንያት ከመጾም ወደኋላ ማለት ራስን ማታለል ነው።

በግሌ እጾማለሁ የሚለኝ የኦርቶዶክስ አማኝ ሲያጋጥመኝ… በጾሙ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጥም። ነገር ግን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ይዤው እገባለሁ። ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እውቀት፣ እምነትና ማስተዋል እንወያይበታለን። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ጾም ምን እንደሚመስልም ሰፋ አድርጌ እወያያለሁ። ይህ ስለወንጌል ሊያነጋግሩኝ የማይፈልጉትን ሁሉ በጽሞና እንድነጋገር ሲያደርገን አስተውያለሁ። ጾምና ጸሎት ጌታን ኢየሱስንና ቃሉ ከማወቅና ከማመን ጋር ካልተያያዘ የረሃብ አድማ ነው።

ስንቱ የኦርቶዶክስ ተውሃዶ ቤተሃይማኖት አባል ነው አቢይ ጾምን ለምን እንደሚጾም የሚያውቀው። ባለሁበት አገር አቢይ ጾምን የምትጾም አንዲት ኢትዮጵያዊት በሥራ ምክንያት ገጥማኝ ሰሞኑን አናግሬ ነበር። በአቢይ ጾም ምክንያት ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ ዝርዝር ውይይት ስንገባ ስለጌታ ኢየሱስ ያላት እውቀት ከታምረ -ማርያም ያነሰ ሆኖ አገኘሁት። በታምረ -ማርያም ላይ ያላትን እውቀት መሠረት አድርጌ ነው ስለጌታ ኢየሱስ መነጋገር የቻልነው። ውይይቱ የሳባት ይመስለኛል፤ ዛሬም እንዲሁ በሥራ ምክንያት ተገናኝተን ውይይታችንን ቀጥለንበት ነበር። ነጥቤ፦ አብዛኛው ይህንን የአቢይ ጾም የሚጾመው የኦርቶዶክስ ቤተሃይማኖት አባል… ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ይህቺ የተማረች ኢትዮጵያዊት ስለኢየሱስ ያላት እውቀት በጣም ትንሽ ነው። ታዲያ ጾሙ እንዴት ሆኖ ነው የሚለውጣት ? መንፈሳዊ ፍሬ እንድታፈራ የሚያደርጋት ? ችግሩ ያለው እዚህ ላይ እንጂ ቀን ቆጥሮ ጾም ነው አልበላም ማለቱ ላይ አይደለም።
_________________
በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና
መጽሐፈ መክብብ 7፡9
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ናጁ .

ኮትኳች

Joined: 23 Aug 2006
Posts: 336

PostPosted: Fri Feb 19, 2010 5:01 am    Post subject: Reply with quote

ብሩክ ነህ ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ ሥላሴ - አሜን ::

በክርስቶስ ደም የተዋጃች , ከሀጢአት ወደ ጽድቅ - ከጨለማ ወደ ብርሀን - ከህይወት ወደ ሞት , ከግራ ወደ ቀኝ በፍቅሩ ያሻገራች ክርስቲያኖች - በድጋሚ እንኩዋን ለጾሙ በረከት አደረሳችሁ ::

ክርስቲያኖች ሲጾሙ - ሰይጣንና አገልጋዮቹ ደግሞ ፈተናቸውን ያጠብቃሉ :: ምክንያቱም ...." እንደነሱ አይነቱ አጋንንት ከጾምና ከጸሎት በቀር አይወጣም " ተብሏልና , ጾምና ጸሎት ለመናፍቃን ራስ ምታት ናቸው ::

ለዚህም እኮ ነው - ላለመጾም ስለፈለጉ ብቻ "እኔ የምጾመው ለጌታ ነው ባደባባይ አይደለም " በማለት ያገኙትን 365 ቀን የሚበሉት :: ለዚህም ነው .. ደሞ ሀሳባቸውን ቀየር ያደርጉና ... የነሱ አለመጾምና ለሆድ መገዛት ሳያንስ የሌላው መጾም ስለሚያናድዳቸው "ወደ ሆድ የሚገባ አያረክስም " ተብሏል እያሉ ለምን ትጾማለህ ? ለማለት የሚዳዳቸው :: ... ለዚህም እኮ ነው , ደግሞ አንዳንዴ በዚህኛው አላስኬድ ሲላቸው ... "ክርስቶስ እኮ የጾመው 40 ቀን ብቻ ነው , እናንተ ለምን 55 ቀን ትጾማላች ? ሲሉ የሚደመጡት ::

በማስተዋል ስናያቸው .. ሶስቱም ክርስቲያኖችን ለማዘናጋትና ከጾምና ከጸሎት ለመለየት ሰይጣን የሚጠቀምባቸው መንገዶች ውስጣቸው ገለባ ናቸው :: የሚገርመው ጌታችንም በጾም ላይ ሳለ , ሰይጣን እንዲሁ 3 ጥያቄዎች አቅርቦ ነበር ሊፈታተነው የሞከረው , ዛሬም የሰይጣን የሆኑቱ የክርስቶስ የሆነነው እኛን እንዲሁ በሶስት ነገሮች (ከላይ በጠቅስኩዋቸው ) ሊፈታተኑን ይሞክራሉ ::

"እስከመጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል " ነውና በፈተና እየተሰነካከልን እንዳንወድቅ ከጌታችን ልንማር , ሰይጣንንም "ሂድ አንተ ሰይጣን " ልንለው ያስፈልጋል ::

ለዚህም ነው ፕሮቴስታንቶች (መናፍቃን ) ምን እንደሚያምኑ የማያውቁ , ግራ የገባቸውና እጃቸውን ለሰይጣን የሰጡ ሆነው የምናገኛቸው :: በፍጹም በአንድ ነገር ላይ አንድ ዐይነት እምነት የላቸውም :: አሁን ያሉትን አሁን ይክዳሉ , ለነሱ ትልቁ ነገር , ዋሽቶና ቀባጥሮ ክርስቲያኖችን ወደነሱ ካምፕ ማስገባት ነው ::

ስለ ጾም ሲነሳ ... መጀመሪያ የጾም ደጋፊ ለመምሰል ይሞክሩና .. ጾምማ ጥሩ ነው .. እኛም እኮ እንጾማለን .. አታውቅም እንዴ ? እንደናንተ ከጠዋት ጀምረን 13 ዐይነት የጾም በያይነቱ እየበላን አይደለም .. በማለት ስለኛ እኛ ሳይሆን እነሱው ሊናገሩልን ይሞክሩና ይኮፈሳሉ ::

ስለኛ እኛው እንናገር ግን እናንተ መቼና የት ነው የምትጾሙት ? ሲባሉ .. እኛ ከጌታ አንድ ነገር ስንፈልግ በቃ ማንም ሳያውቅ እንጾማለን .. አየህ እሱም እኮ ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ ብሏል .. በማለት የማይገናኙ ጥቅሶችን መጥቀስ ይጀምራሉ ::

እኛ እንደነሱ በማጣጣልና በማራከስ አንጀምርም :: ጥሩ ነው , እንደአፋች ያርገውና መጾማችሁ ጥሩ ነው , ግን እናንተ የምታወሩት አንድ ክርስቲያን ከአምላኩ ጋር ተነጋግሮ ለተለየ ሰጦታ ወይም ጥያቄ ሌላው ሳያውቅ ሊጾም ይችላል :: እሱ ችግር የለውም :: ነገር ግን በማህበርና በህብረት የጾም ጊዜ ወስኖ መጾም ደግሞ ያስፈልጋል :: ያንንም መጽሀፍ ቅዱስ አንድ ቦታ "ጾምን አውጁ - ጉባኤውንም ቀድሱ " ሲል ሌላ ቦታ ደግሞ የነነዌ ሰዎች በአዋጅ በህብረት መጾማቸው , ሌላ ቦታ ደግሞ "ሙሽራው ከነሱ የሚለይበት ጊዜ ይመጣል , በዚያን ወራት ይጾማሉ " ሲል ክርስቶስ መናገሩ ... ቅዱስ ጳውሎስም "የጾም ወራት ባለፈ ጊዜ .." በማለት የጾም ወር የሚባል ወቅት መኖሩን ተናግሯል - ታዲያ እንዚህ ሁሉ የህብረትና የአዋጅ ጾም ስለመኖሩ የሚናገሩ አይደሉምን ? ስንላቸው .. .... ሁሉንም ይተዉና ... የነነዌ ሰዎች የጾሙት ያን ጊዜ ችግር ስለነበረ ነው .. በማለት "አሁን ችግር በዐለም ላይ ስለሌለ ጾም አያስፈልግም " የሚል ስሜት ያለው መልስ ይሰጣሉ ::

በአንድ በኩል "እኛም እኮ እንጾማለን " ብለው የጀመሩት ጉንጭ አልፋ ክርክር .. ሳይስቡት ጾምን በመቃወም ሞቅ ይላል :; ሳያስቡት የጾም ተቃራኒ ይሆናሉ ::

ብቻም አይደለም .... የነሱ አለመጾም አንሶ .. ትንሽ ጊዜ አብሮ ለቆያቸው ሰው ..ይህን አልበላም እጾማለሁ ካላቸው .. እነሱም መልሰው "ወደ ሆድ የሚገባ አያረክስም - ዝም ብለህ ብላ " ማለት ይጀምራሉ ::

ጥቅሱ የተጠቀሰው እጅን ታጥቦ ስለመብላትና ስለ አለመብላት ቢሆንም እነሱ ጾምን ለመቃወም ይጠቅሱታል :: የዚህ ቃል ትርጉም በደንብ ሲብራራላቸው ደግሞ እንዲህ ይላሉ ....... "ባክህ ወግ አታጥብቅ . ጌታ የጾመው አርባ ቀን .. እናንተ 55 ቀን .. ለመሆኑ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ 55 ቀን ጹሙ የሚል አለ ?" በማለት ይጠይቃሉ ::

ሰይጣን ካለሆነ በቀር ለምን አርዝማች ትጾማላችሁ የሚል ሊኖር አይገባም ነበር :: እንኩዋን 55 ቀን 55 አመት ብንጾምስ ? .. ይልቁኑ 40ውን ቀን ቀንሰን 35 ብናደርገው .. ያኔ ነበር "ለምን ቀነሳች ?" የሚል ጥያቄ ቢነሳ የሚያምረው ?

በዚያም ሆነ በዚህ ግን አላማው ጾምን ማስቀረት , "ሆዳቸው አምላካቸው ነው " እንዳለ , ሆድን አምላክ ማድረግ ነው :: እኛ ለጌታ ነግረን እንጾማለን እያሉ ይናገሩ እንጂ አንድም መናፍቅ ጾም የሚባል ነገር እንደማያውቅ መናገር ይችላል :: እንዲያውም ድርጅታቸው ጾም እንጀምር ቢል ብዙዎች ጥለው ሊወጡ ሁሉ ይችላሉ ::

ጾም ከጌታ የተሰጠን ሰይጣንን ድል ከምንነሳበት መሳሪያ አንዱ ነው :: እኛ እንጾማለን - መናፍቃን - ምን እንደሚያምኑ ስለማያውቁ ... እንደ ፈለጉ ይብሉ :: እኛ አገራችን በሰማይ ነውና ከላይ የሚመጣውን እንጠብቃለን - እነሱ ሀሳባቸው ምድራዊ ነውና ለስጋቸው የሚሆነው ላይ ያተኩሩ ::

ይቆየን ::

_________________
http://www.ethiopianorthodox.org/

http://www.saveethiopians.net/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ናጁ .

ኮትኳች

Joined: 23 Aug 2006
Posts: 336

PostPosted: Fri Apr 02, 2010 2:49 am    Post subject: Reply with quote

biruk neh geta እንደጻፈ(ች)ው:
በሰመ ስላሴ !

አዎ ጀመር እንዳደረግነው መናፍቃን በተለይም ፕሮቴስታንቶች ምን እንደሚያምኑ ካለማወቃቸው የተነሳ ለሚናገሩት ነገር እንኩዋን የሚጠቅሱት ጥቅስ የማይገናኝ - እንዲሁ አፋቸው ላይ የመጣውን ሁሉ ነው ::

ለዚህ ነው እውቀት በሌላቸው ዘንድ እንዳዋቂ ተደርገው የሚቆጠሩት :: የህክምና እውቀት ባልነበራቸው በአያቶቻችን ጊዜም እኮ የመንደር ጥርስ ነቃይ እንደ ተአምረኛ ዶክተር ይቆጠር ነበር :: "ዶክተር መጡ !" ነበር የሚባለው ::

ዛሬም ይኸው ነው :: ጥቂት የመጽሀፍ ቅዱስ እውቀት ላለው ሰው ፕሮቴስታንቶች እምነታችን ብለው የሚናገሩት ነገር እጅግ አሳፋሪ ነው :: ከትልቁ የክህደት ትምህርታቸው እንጀምር - አማላጅነት ::

በመናፍቃን መንደር ስለ አማላጅነት ሲነሳ እንዲህ ይላሉ .. "አማላጃችን ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው - ሌላ አማላጅ የሚባል ነገር በፍጹም የለም !" .......... ይህ እንግዲህ ሁሉም ማለት ይቻላል የሚስማሙበት ነው :: እዚሁ ጋር እንቆይ እና የምታውቁዋቸውን ጠይቁዋቸው :: መልሳቸው አዎና ! ነው :: ጥቂት ቆይተው ጥያቄው ጠበቅ ሲልባቸው ደግሞ ምን እንደሚሉ እንይ .....

ይቀጥላል ::

_________________
http://www.ethiopianorthodox.org/

http://www.saveethiopians.net/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8
Page 8 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia