WARKA Forum Index
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 
Become a supporting member
CyberEthiopia Home | About us | Contact us
ዝንቅ
Goto page 1, 2  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Wed Jan 27, 2010 10:08 am    Post subject: ዝንቅ Reply with quote

ታሪክ ህልም አይደለም ይልቁንም ባንድ ወቅት በግሀድ አለም የነበረ ነባራዊ እውነታ ነው :: ሰዎች ታሪክን ለመመለስ ብዙ ጥረቶችን ቢያደርጉ አስመስለው መስራት ካልሆነ በቀር ያንኑ ታሪክ በእውነታው ዳግም ሊያደርጉት ፍጹም አይችሉም :: ህልም ደግሞ በአእምሮ የተቀረጸ የሌሊት ሀሳባዊ አለም ሲሆን አንዳንዴ በግሀድ የነበረ ሲሆን አንዳንዴ ፍጹም ሀሳባዊ ብቻ ሆኖ ይቀራል ::እኔም እነኝህ ሁለት የተለያዩ ገጽታዎችን ባልለዩ ቡድኖች ገብቸ ለማስረዳት የፈጀብኝ ጊዜ በቀላል የሚገመት አልነበረም ::ጊዜው የበጋ ወራት ሲሆን ሀይለኛው ጠራራ ጽሀይ መላ አካላትን ያቃጥላል በረድፍ የሚጝኣዙት የእቃ መጫኛ ካሚዮኖች ሰዎቹን በእቃ ፋንታ ጭነው ይከንፋሉ የጭነት መኪናዎቹ ብዛታቸው ወደ 10 ሲደርሱ አንዱ ሌላውን በጎማዎቹ በሚፈልሰው አቧራ እያለበሰ ርቀታቸውን ጠብቀው ሲጓዙ ውለው ወረታ ሲደርሱ የካሚዮኖቹ ሹፌሮች ምሳ ለመብላት ለረፍት ያቆሙና ከላይ ያሳፈሯቸውን መንገደኞች ወርደው እንዲናፈሱ 15 ደቂቃ እረፍት እንዳላቸው ነገራቸው :: በዚህ ስአት እኔ ከገጠር ወደ ባህር ዳር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት እማር ስለ ነበር አውቶስ ስጠብቅ ውየ አውቶብስ የማገኝበት ስአት ስለተመናመነ መኪና በመጣ ቁጥር ስንቅ የያዝኩባትን አገልግል ይዥ ወደ መጣው መኪና ሁሉ እበራለሁ የእነዚህን ካሚዮኖች ድምጽ ገና ስሰማ ባለ በሌለ ህይሌ በረርኩ ስደርስ ግን የተጫኑትን የሰዎችን ቁጥርና አቧራ መልበሳቸውን ሳይ በጣም ደነገጥኩ ;ምክንያቱም በወቅቱ ደርግ ሰዎችን በሀይል ከገበያ እያፈሰ ውትድርና የሚወስድበት ወቅት በመሆኑ : ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ የሚወሰዱ ሰዎች ስለመሰሉኝ "አታጣልፈኝ " አልኩት እራሴን በሆዴ እየፈራሁ : ልብ ስል ግን ህጻናቶች :ሽማግሌዎች :የቤት እቃ ቅሉን ቓንቁራውን :ሰፌድ : ሰበጥራውን ስመለከት ልቤ ተረጋጋና ወደ አንደኛው ሾፌር ተጠግቸ "ጋሸ እስከ ባህር ዳር ድረስ ሊያሳፍሩኝ ይቸላሉ ?" አልኳቸው ሾፌሩም " ትከእፍላለህ " ሲሉኝ እኔም ቀበል አድርጌ " ስንት ?" ስላቸው " 2 ብር " ሲሉኝ እሺ ብዬ በቀኝ በኩል ባለው መሰላል ቁብ ቁብ ብየ ተሳፈርኩ :: በዚህ ስአት ፍጹም ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር ተደባለቅኩ :: ልቤ በጥያቄ ተሞላ እነኝህ ሰዎች እነማን ናቸው ? ከየት ነው የመጡት ? የት ነው የሚሄዱት ? ለምን ህጻናት ሽማግሌዎች ተጨመሩ ? ሰፈራጣቢያ ይሆን የሚሄዱ ? ወይንስ መንደር ምስረታ ነው ? ማንን ልጠይቅ ?
ምን ብዬ ልጠይቅ ? በዚህ ሀሳብ ላይ እንዳለሁ ካሚዮኑ ተንቀሳቀሰ :: ይቀጥላል >>>>>>>>>>
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

Debzi

ዋና አለቃ

Joined: 02 May 2004
Posts: 2770
Location: Los Angeles, CA

PostPosted: Sun Jan 31, 2010 2:59 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ቻላቸው ,

ቀጥለው እስቲ ጥሩ ታሪክ ይመስላል ::
_________________
Ke akbrot selamta gar!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

MIMI77

ዋና ኮትኳች

Joined: 31 Jan 2010
Posts: 553

PostPosted: Sun Jan 31, 2010 8:11 am    Post subject: Reply with quote

Debzi እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ቻላቸው ,

ቀጥለው እስቲ ጥሩ ታሪክ ይመስላል ::

ምነው እቴ Rolling Eyes አሉ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ባሻ ብሩ

ውሃ አጠጪ

Joined: 12 Feb 2005
Posts: 1368
Location: ዋርካ ቦተሊካ

PostPosted: Sun Jan 31, 2010 7:03 pm    Post subject: Reply with quote

ቻላቸው አሻንጉሊቱ ! Laughing
ይህን ክፍል ረስተኸው ነው አይደል ? በል ናና ጨርስ እየጠበቅን ነው ::
_________________
May God have mercy up on my enemies because I won't.
General George S. Patton
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Sun Jan 31, 2010 8:13 pm    Post subject: Reply with quote

ሲበር የመጣን አህያ አጥብቀህ ጫነው አይደል ነገሩ : እኔም ከነሱ ባላነሰ እንዳውም በካሚዮኑ ዳር ተንቆራጥጨ በጣም የሚያንገበግበውን ሙቀት ከንፋስ ጋር እያራገበና እያንቦጀቦጀ በፍጥነት ከነሱ ጋር ሊያመሳስለኝ የቸኮለ ይመስል ባንዴ አቧራ ሁለንተናየን አላበሰኝ ሁላችንም ባንዴ ተመሳሰልን : ካሚዮኑ ፍጥነቱን ጠብቆ ያጣድፈናል እኔም እንደነሱ አቧራየን እየማግኩና እየለበስኩ ብሄድም እነሱ የት እንደሚሄዱ ሲያውቁ እኔ ግን እነሱ የሚሄዱበትን አለማወቄ ውስጥ ውስጤን እያብላላው ማንን ልጠይቅ ? በሚለው ጥያቄ ውስጤ ተወጥሯል የጉዞውን አለመመቸት ሳይሆን ያሳሰበኝ የሰዎቹ ማንነት ማወቅ ነው ውስጥ ውስጤን ያሳሰበኝ : ለዚህም ነው አይኔ ያለማቋረጥ የምጠይቀው ሰው ፍለጋ የሚቀላውጠው : ከሰዎቹ ወሬ ፍንጭ ለማግኘት ብሞክርም ከሚያውሩት ወሬ ስለማንነታቸውና ስለጉዟቸው አላማና ቦታ ወሬ ፍጹም ቅንጣት ፍንጭ እንኳን ማግኘት አልቻልኩም አንድ ነገር ለማድረግ ወሰንኩ ያም ባቀማመጡ ወደኔ የቀረበውን ወጣት መጠየቅ ::
ለወሬ መጀመርያ አፍ መክፈቻ " ምን አይነት አቧረ ነው ባክህ ?
ልጁም መልሶ " አቧራው ምን አለው ብለህ ነው እኔን ያስመረረኝ ነፋሱ ነው ባክህ " እያለ አቧራ በጠገበው ኩታ እራሱን ይሸፍናል :: እኔም መልሸ ወሬአችን እንዳያቖርጥ
"የት ተነስታችሁ ነው ይህንን ያህል ሁለንተናችሁ እንዲህ አቧራ ብቻ የሆናችሁ ?" ፈገግ ብሎ " አንተ እራስህን አይተኸዋል ?' አለ ፊቱን ወደ ሽማግሌው ዞር ብሎ ለጥያቄየ መልስ ለመስጠት ፈቃድ ከሽማግሌው የሚጠይቅ ይመሰል ግን ሽማግሌው ወሬአችን አለማዳመጣቸውን ካረጋገጠ በሁዋላ " ከዳባት ተነስተን ነው የመጣነው " ሲል መለሰልኝ እኔም ቀጠል አድርጌ "ወደየት ነው የምትሄዱት ? "
" አንተ ወደየት ነው የምትሄደው " ሲል መለሰልኝ
እኔም የከተሞችን ስም ስለማያውቅ ይሆናል ብዬ ለምርጫ እንዲመቸው ስል " ሀሙሲት ; ባህርዳር ደብረማርቆስ ;ፍኖተሰላም ; አዲስ አበባ : አልኩት
ልጁም መልሶ :" እኛም እዛው ነው የምንሄደው " ብሎኝ እርፍ ::
አይኔ በጥልቁ ያረፈው ግን ባንዲት የነጠላዋን ጫፍ ባፏ ነክሳ የያዘች የአይንዋ ጭራ በአቧራ የተሸፈነ ሁለንተናዋ ከንፋሱና ከአቧራው ጋር ከምተተገልና ሳስተውላት ሀሳብ ጭልጥ አድርጎ የወሰዳት ከምትመስል ከሁሉም ነገር እራስዋል አግልላ በራስዋ አለም የምትከንፍ ከምትመስለው ወጣት መልስ የማገኝ ይመስል አይኔ ክፉኛ ማንንም ሚዛን ውስጥ ግምት ሳያስገባ በድፍረት ተወረወረ እስዋ ግን ማንንም አትመለከትም እኔም በልቤ ምናልባትም ከቤትዋ ወጥታ የማታውቅ ሆና ይሆን ይህንን ያህል በሀሳብ የሰመጠች ስል ራሴን በራሴ ጠየቅኩት ;: ይህንን ሁሉ የከበባትን መሰናክል አልፌ እንዴት እንደምጠይቃት አእምሮየ መላ ማውጠንጠን ቢጀምርም ልቤ ግን ድፍረት አጣና ለፍርሀቴ ማገገሚያ ግን አጠገብዋ ያሉትን ሸማግሌ "የት ነው የምትሄዱ ?" ብየ ጠየቅኳቸው ?" ምነው አብረኸን ልትሄድ ፈለግክ እንዴ ?: ሲሉኝ
እኔም : 'አብሬ እየሄድኩ አይደል እንዴ ? "
ሽማግሌውም መልሰው " አብረህን ከሄድክ የምትሄድበትን ሳታውቅ ነው እንዴ የምትሄደው ?' ሲሉኝ አኡፍ ስል በጥብቁ ተነፈስኩ :;
በንዲህ ሁኔታ ላይ እያለን ነው ያባይን ድልድይ ስንሻገር አቧራውም ነፋሱም ብርድ ያለልን :: ይቀጥላል .........................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Sun Jan 31, 2010 8:15 pm    Post subject: Reply with quote

ከዛስ ?..ወሬየን እስኪ ላውራበት ? ይህንን የዝንብ ወተት ደርሶ ጥልቅ ባዩን ባሻ ነኝ ባዩን ወደዛ ፈቀቅ አድርጉልኝ
ወገኖቸ
ወይ ጉድ ? ባሻ ወደ ውጭ ወጣ በልና እስኪያልፍልህ ድረስ ትንሽ ዘወር ዘወር ብለህ እሺ
ባሻ : እምቢቢቢቢቢቢቢ !!!!!!!!!!!!!!!!

ጨቅጫቃ !!!!!!!!!!!!!!!!!ሙጫ !!!!!!!!!!!!!!!
ሂድ ጥፋ ከፊቴ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ድሮም አንተ ክብር አይወድልህም ወግድልኝ

Last edited by ቻላቸው on Wed Feb 03, 2010 8:21 pm; edited 3 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Mon Feb 01, 2010 12:33 am    Post subject: Reply with quote

ባሻ ብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
ቻላቸው አሻንጉሊቱ ! Laughing
ይህን ክፍል ረስተኸው ነው አይደል ? በል ናና ጨርስ እየጠበቅን ነው ::
እዩት እንግዲህ ይህንን ነገረኛ ምነው ሊቁ ባሻ ብሩ ? ተወኝ አላልኩህም ይህንን ደርሶ እንደዝንብ ወተት ጥልቅ ማለት ? ወይ ጉድ አሁን እንዲህ በጣም የምትወተውተኝ እድገት እየሰጠህኝ መስሎህ ነው ወይንስ አውርጀ ዘጭ ያደረግኩት እየመሰለህ ነው ? አንዴ ሮቦት ሌላ ጊዜ አሻንጉሊት ስም እየለዋወጥክ የምትዘልፈኝ ጃል ? መቸም ነገርን ነገር ያነሳዋል አይደል ትላልቆቹ እንደሚሉት ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ነውና አንድ ምስሌ ላንተም ላንባቢም ልጻፍ
አንባብያን አንዴ ይቅርታ ርሴን አስለቀቀኝ ቢሆንም ምሱን ካልቀመሰ እየወተወተ አያስጽፈኝምና ምሱን ነግሬ ትንሽ ላሳርፈውና ወደጀመርኩት እመለሳለሁ በትእግስት ጠብቁኝ ባሹ በል ምስህን ቶሎ ቶሎ ሳታቋርጥ አንብባትና ፈውስን ትሰጥ ሀለችና ሳታቋርጥ አንበባት ጎሽ የኔ ባሻ ..................
ኬንያ የእንስሳት ማስጎብኛ ክልል ውስጥ ለጉብኝት አንድ ቱሪስት ገብቶ ይጎበኛል :: ብዙ እንስሳቶች ከደስታ ብዛት ይቧርቃሉ ይፈነጥዛሉ :ከእንስሳቶች ሁሉ በተለየ ሁኔታ አህያ ብቻ ተጎንብሶ ሰርዶውን እየጋጠ ባካባቢው የሚደረገው ጭፈራና ደስታ ምንም መስሎ አይታየውም በዚህ ሁኔታ የተገረመው ጎብኝ ነገሩን እያብሰለሰለ
ወደማረፍያ ቦታው ተመልሶ ሄደ :: በማግስቱ ጥዋት ዳግም እዛው ቦታ ለጉብኝት ገባ : የተመለከው ግን ከትላንቱ የተገላቢጦሹን ነበር ያም አህያ እያነፏና እየዘለለ ሌሎቹ ግን ምግባቸውን እየበሉ ያያቸዋል :ጎብኝው ምክንያቱን ለመረዳት ወደ አስጎብኝዎች /ቤት
ገብቶ ያየውን ሁሉ ያጫውታቸዋል :አስጎብኝውም የጎብኝወን አስተዋይነት አድንቀው እንዲህ ሲሉ ሁኔታውን ለጎብኝው አስርዱ " ትላንት ጦጣ በጣም የሚያስቅ ቀልድ ለእንስሳቶች ሁሉ ቀልዳ ነበር የቀልዱም መልእክት በወቅቱ የገባቸው ሁሉ በጊዜው ሲሰቁ ነው አንተ የደረስከው : አይገርምህም ባሻ አህያ ግን ዛሬ የሚናፏው ትላንት ጦጣ የቀለደችው ቀልድ 24 ስአት በሁዋላ ስለገባው ነው :; ሲሉ አብራሩለት ይባላል ::
ባሹ ሌላ እንስሳ 24 ስአት በሁዋላ ነገር የሚገባው አለ . ???? ደግመህ አንበበው ይህእውና ላንተ 2 ጊዜ ልድገምልህ ቢገባህ Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing

Last edited by ቻላቸው on Wed Feb 03, 2010 9:29 pm; edited 6 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Tue Feb 02, 2010 4:26 am    Post subject: Reply with quote

የባሽየን ቁርስ ሰጥቸ ተመለስኩላችሁ መቸም 'በጥባጭ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል ' አይደል ነገሩ ከበጥባጩ ባሻ በፊት ካለው ትረካ የሚቀጥል ነበር ዳሩ ምን ያደርጋል እንዳንዳንድ ባለጌ ካፍ ጥልቅ ባይ ዝንብ የዋርካው ዝንብ ባሻ ጥልቅ ሊል ቢሞክርም እድሜ ለበሬ ጭራ ያበነዋል አልበገርለትም ......... ቀጣዩ እንዲህ ነበር ________--------------------------------- ቀኑ ሊመሽ ጀንበር አዘቅዝቃለች በባህር ዳር ከተማ መግቢያ በጥርጊያው ረድፍ ያሉት የዝንባባ ዛፎች ጥላ በጥቁሩ አስፓልት ላይ ልክ በቡና አይነት ክላሰር ላይ በጥቁር ቀለም እንደተሳለ የዝንባባ ሰእል አልፎ አልፎ ይታያሉ : በጥርጊያው ግራና ቀኝ በብስክሌት ወንድ ሴት ;ወጣት ;ጎልማሳ ;ሳይል በተለያየ አቅጣጫ ይጓዛሉ ;: እንደ ሰርዲን የታጨቁት የካሚዮኑ ተጫኞች (ተሳፋሪዎች ) እንደ ደመራ ሹግ ሁሉም ቀጥ ብለው ቁመው ሁሉም አይናቸውን ከላይ ወደታች አፍጥጠው ይመለከታሉ ; ባህር ዳርም ያሳለፍነውን አስልች ጉዞ ለማስረሳት ያላትን ውበት ሁሉ ገልጣ እዩኝ እዩኝ ትላለች :: ከታች በጥርጊያው ዙርያ ያሉት ሰዎች ሁሉ ከብዛታችን ይሁን ካቧራችን ካሚዮኑን ያየ ሁሉ አተኩሮ ይምትለከተናል ::
ሁሉም ካሚዮኖች እየተከታተሉ ካውቶብስ ማረፊያው አጠገብ ካለው ትልቅ ሜዳ ላይ ሁላችንም አወረዱን :: ገና በመሰላሉ በመውረድ ላይ እያለሁ ሹፌሩ ከታች ይጠብቀኛል እኔም ነገሩ ስለገባኝ የመጣሁበትን 2ብር ሊቀበል እንደሚጠብቀኝ አውቄ 2ብር ከኪሴ አውጥቸ ሰጠሁት :የሚገርመው ግንግር ብሎኝ አብሬአቸው የተጓዝኩትን ሰዎች ሳልሰናበት ወደ መኖርያ ቤቴ አመራሁ :: አንገቴን ደፍቸ በራሴ ውስጣዊ ሀሳብ ተመስጨ የነገ ትምህርቴን እያውጠነጠንኩ ወደ መኖርያ ቤቴ ስሔድ በድንገት አንድ ነገር መርሳቴን አስታወስኩኝ : ወላጅ እናቴ ሌት ደሮ ሲጮህ ቀደም ብላ ተነስታ ምጎጎዋን ጥዳ ;በጢስ እየታፈነች እንጀራ ጋግራ ወጥ ሰርታ ትኩስ ትኩሱን እጥፍ እጥፍ እያደረገች በሰፋችው አገልግል የቋጠረችልኝን የሳምንት ስንቄን : በዛች የነጠላዋን ጫፍ ባፍዋ በነከሰችና ቀልቧ በተሰወረ ኮረዳ : የኔም ቀልብ ተሰወሮ ያለስንቅ ባዶ እጀን ወደቤቴ እየሄድኩ መሆኔን ሳስተውል በመጣሁበት መንገድ ተመልሸ እግሬን አንስቸ ወደካሚዮኑ በረርኩኝ :; ይቀጥላል -----

Last edited by ቻላቸው on Wed Feb 03, 2010 9:42 pm; edited 15 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Tue Feb 02, 2010 4:32 am    Post subject: Reply with quote

Exclamation Exclamation ይጠንቀቁ Exclamation Exclamation የዝንብ ማጥፊያ የተረጨ አካባ Exclamation Exclamation Exclamation ዝንቡ አንዳትገባ Exclamation Exclamation Exclamation
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Thu Feb 04, 2010 5:43 am    Post subject: Reply with quote

መንገድ አይኑ ይጥፋ አይባልም ደርሶ : የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ : ሆነና እኔም በሄድኩበት መንገድ አገልገሌን ላተርፍ እየተንደፈደኩ ስሮጥ ፊት ለፊቴ እናቴ የሰነቀችልኝን አገልገል የያዘችው ጉብል ጋር ግጥም :ለካስ ያገልግሌን መርሳት ያስተዋሉት ሽማግሌ ያችን ካሚዮኑ ውስጥ አይኔ ያረፈባትን ጉብል "" ዝናሽ ይህ ያስኳላ ተማሪ አገልግሉን ጉም አድርጎት ሄደ አረ እባክሽን እሩጭና በሄደበት ተከትለሽ ሥጭው ይህስ ደግሞ ከኔ ከሽማግሌውም የባሰ ነው "" ብለው የሰደድዋት ጉብል እስዋም ወደኔ እየበረረች እኔም ወደአገልግሌ እየበረርኩ
መሀል መንገድ ላይ ግጥም :;
ቀና ብየ ሳያት መላው አከላቴን አንዳች ነገር ወረረው መላው ሰውነቴ ናረ :አንደበቴ ተሳሰረ ጉልበቴም ፈሰሰ የምሆነው የማደርገው ጠፋብኝ "" አመሰግናለሁ !"" አልኩዋት ""አይ እኔ ሳልሆን አባ አጥናፉ ናቸው አድርሽለት ያሉኝ "" ስትለኝ ""አባትሽ ናቸው ? "' ብላት
"" አርሳቸው እኮ አባቴ አይደሉም "" አለችኝ
እኔም "" ታድያ ምንሽ ናቸው ? "' ዘመዴ "'
ዝናሽ ቃልዋ እየተቆራረጠ በል ደህ --ሁን "" ብላኝ ወደመጣችበት ልትመለስ እየቃጣት ዘወር ማለት ስትጀምር ""ቆይ እስኪ የትኛው ሰውየ ናቸው ታድያ ያንቸ አባት ? "' አልኳት
"" አባቴማ ገጠር ነው የቀረው "" እናትሽስ ? "" እናት የለኝም ""
"እንዴት ? ሰው እናት አልባ ይፈጠራል አንዴ ?" ስላት አይ እናቴ በልጅነቴ ነው የሞተችብን " አለችኝ ;:
ዝናሽ : "በል ልሂድበት እቸኩላለህ " የት ነው የምትሄጂው ? ' " ከመኪናው ነዋ ' አለችኝ ውሽክ ብላ ያኔ ነው አጋጣሚ አስገደዶ ካንዴም ሁለቴ ካገናኘን አስገድዶማ አይለያየንም ብየ የራሴን አንድ እርምጃ ልከተላት የወሰንኩኝ :: "በይ እኔም መጣሁ
አባ አጥናፉን አገልግሌ እንዳይጠፋና አንችንም ስለላኩልኝ እግዛብሄር ይስጥልኝ ልላቸው " ብየ በሰበቡ ተከተልኳት :: ይቀጥላል .....................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Fri Feb 05, 2010 11:48 am    Post subject: Reply with quote

[quote="ቻላቸው "]መንገድ አይኑ ይጥፋ አይባልም ደርሶ : የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ : ሆነና እኔም በሄድኩበት መንገድ አገልገሌን ላተርፍ እየተንደፈደኩ ስሮጥ ፊት ለፊቴ እናቴ የሰነቀችልኝን አገልገል የያዘችው ጉብል ጋር ግጥም :ለካስ ያገልግሌን መርሳት ያስተዋሉት ሽማግሌ ያችን ካሚዮኑ ውስጥ አይኔ ያረፈባትን ጉብል "" ዝናሽ ይህ ያስኳላ ተማሪ አገልግሉን ጉም አድርጎት ሄደ አረ እባክሽን እሩጭና በሄደበት ተከትለሽ ሥጭው ይህስ ደግሞ ከኔ ከሽማግሌውም የባሰ ነው "" ብለው የሰደድዋት ጉብል እስዋም ወደኔ እየበረረች እኔም ወደአገልግሌ እየበረርኩ
መሀል መንገድ ላይ ግጥም :;
ቀና ብየ ሳያት መላው አከላቴን አንዳች ነገር ወረረው መላው ሰውነቴ ናረ :አንደበቴ ተሳሰረ ጉልበቴም ፈሰሰ የምሆነው የማደርገው ጠፋብኝ "" አመሰግናለሁ !"" አልኩዋት ""አይ እኔ ሳልሆን አባ አጥናፉ ናቸው አድርሽለት ያሉኝ "" ስትለኝ ""አባትሽ ናቸው ? "' ብላት
"" አርሳቸው እኮ አባቴ አይደሉም "" አለችኝ
እኔም "" ታድያ ምንሽ ናቸው ? "' ዘመዴ "'
ዝናሽ ቃልዋ እየተቆራረጠ በል ደህ --ሁን "" ብላኝ ወደመጣችበት ልትመለስ እየቃጣት ዘወር ማለት ስትጀምር ""ቆይ እስኪ የትኛው ሰውየ ናቸው ታድያ ያንቸ አባት ? "' አልኳት
"" አባቴማ ገጠር ነው የቀረው "" እናትሽስ ? "" እናት የለኝም ""
"እንዴት ? ሰው እናት አልባ ይፈጠራል አንዴ ?" ስላት አይ እናቴ በልጅነቴ ነው የሞተችብን " አለችኝ ;:
ዝናሽ : "በል ልሂድበት እቸኩላለህ " የት ነው የምትሄጂው ? ' " ከመኪናው ነዋ ' አለችኝ ውሽክ ብላ ያኔ ነው አጋጣሚ አስገደዶ ካንዴም ሁለቴ ካገናኘን አስገድዶማ አይለያየንም ብየ የራሴን አንድ እርምጃ ልከተላት የወሰንኩኝ :: "በይ እኔም መጣሁ
አባ አጥናፉን አገልግሌ እንዳይጠፋና አንችንም ስለላኩልኝ እግዛብሄር ይስጥልኝ ልላቸው " ብየ በሰበቡ ተከተልኳት :: የቀጠለ .......................................................
እሷ ፈት ፈት ቀደም ቀደም እያለች በአዲሱ የጎማ ኮንጎ ጫማ ስትራመድ አካሄድዋ ጫማው አዲሷ እንደሆነ ይናገራል ፍጥነትዋ ግን ጥለዋት እንዳይሄዱ ከመስጋትም የመነጨ ይሁን እንጃ አጥብቃ ፈጠነች :: እኔም አገልግሌን በቀኝ እጄ አንዳንጠለልኩ ከኻላዋ በገበሬ ጫማየ ቃዳ ቃዳውን እየተራመድኩኝ ልደርስባት አልቻልኩም ; ይሁን እንጂ እከተላት አለሁ ; አይኔ እሷን እያየ አእምሮየ ግን ወላጆቸን አልባ መንግደኛ ነኝ
ስላለችኝ ዝናሽ : ብዙ ውስብብ ጥያቄዎችን ያምሰለስላል ;:
እንዴት ሰው ገና ልብ ያላወቀን ልጅ እለት እለት በማያዩበት ቦታ : ችግር ቢደርስበት ፈጥኘ እደርሥለታለሁ በማይሉበት ሩቅ በጣም ሩቅ ቦታ ሌላ ሰውን አምኖ እንደ አደራ እቃ መላክ ? ወይ አደፋፈር ! 'ባለቤቱ ያቀለለውን ለቅሶ :" ታድያ አሁን አይበል እንጂ ዝናሽ አንድ ነገር ብትሆን አባ አጥናፉን ማን ነው እንዲህ ሳያርጉላት ብሎ ሊያማቸው የሚችል ? ::
በባህር ዳር የድሮ አውቶብስ ማረፊያ አጠገብ ያለው ሰፊ ሜዳ በሰዎች ብዛት ተጥለቅልቕል : ከየት መጡ ሳይባል የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች ከጥበቃ ጓዶች ጋር መንገደኞችን ; የከተማዋን ጽዳት ታቆሽሻላችሁ በሚል ሰበብ እያጣደፉ በመጡበት ካሚዮኖች አሳፍረው ከከተማዋ ውጭ እረፍት እንዲያደርጉ አስገድደው አሳፍረው አባረሯችው ::
ዝናሽ የፈራችው አልቀረላትም : ካውቶበስ ጣብያው ድርስ አንዳልነ የቦታውን ጭልል ማለት የጉዞ ጓደኞቿን አለመኖር ስትመለከት ግራ ተጋብታ ደነገጠች : ዝናሽ ' አዎይ አለመታደሌ ስትል : ፊትዋን ወደኔ ዞር ብላ በጥያቄ አመለካከት ስትመለከተኝ መልስ ጠፋኝ :: ይቀጥላል ...................................................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Sun Feb 07, 2010 12:02 pm    Post subject: Reply with quote

አባይ ማደርያ የለውም ግንድ ይዞ ይዞራል ነው የሚባል :ዝናሽን እያስከተኩ ሳልወድ በግዴ በየቦታው እየሮጥኩ እዚህ የነበሩት ብዙ እንግዳ ሰዎች ወደየት ሄዱ ? በማለት ያገኘሁትን ሰው ሁሉ አጠያይቅ ጀመር : አንዳንዶቹ ስለምን እንደማወራ ስለማያውቁ እንደሞኝ አይተውኝ በዝምታ ሲያልፉ :አንዳንዶቹ ደግሞ ያዩትን እንዲህ ሲሉ ያስረዱኛል ; የጥበቃ ጓድ የከተማዋን ንጽህና አቆሸሻችሁ ብለው ከከተማዋ ውጭ አባረሯቸው እኮ የት ነበራችሁ ተቋርጣችሁ ቀራችሁ እንዴ ? ሲሉ ከንፈራቸውን በመምጠጥ ሀዘናቸውን ይገልጻሉ : እኔ ልቤ በጣም አዘነ እንዴት የከተማን ንጽህና ለመጠበቅ
ሰውን እንደእቃ አስጥሎ የሚያባርር ጥበቃ ጓድ ... አሉት አቤት ጉድ ድንቄም ትጠብቀው : የሰው ሽንትና እዳሪ መሬት እንዳይወድቅ ከሰብአዊ ደህንነት ጥበቃ የበለጠ ትኩረት የሰጠ ጥበቃ የጠበቃ ጓድ ;;
ይገርምሀል አለኝ አንዱ ሊስትሮ መሀል መንገድ ላይ ከዝናሽ ጋር ስንጓለል ያየኝ ነገሬ ገብቶት አንድ ሽማግሌ ኡኡኡኡኡ ያደራ ልጀን በርሀ በላት እያሉ በዱላ እየዘለጠ ነው ሳይወዱ በግድ ጭነቱ መኪና አስፍሮ የገፈተራቸው (ባራድኛ ቋንቛ ያባረራቸው ) ሊል እንደፈለገ ገባኝ ያኔ ልቤ ቆርጦ ሳልወድ በግድ ዝናን አስከትዬ ወደመኖርያ ዶርሜ ለመህድ ተገደድኩ
አምሽቸ ስገባ የማይወዱትን ቤት ያከራዩኝ / ሙጭቴ መግቢያው በር ላይ ቁመው ሲጠብቁኝ አገኘኻቸው ::
በሩቁ ገና ሲያዩን ከት ከት ብለው ስቀው እሰይ የኔ ጎረምሳ ለዚህ ደረስክ አይደል ዛሬስ ብለህ ብለህ ደግሞ ሴት ይዘህ ግቢያችን ብቅ አልክ እንዴ ሲሉ በለበጣ ጠቆም አደረጉኝ እራስ ሳይጠና ጉተና ሲሉ ከት ከት ብለው ደግመው ሳቁ >>>>>>>>>>>ይቀጥላል

Last edited by ቻላቸው on Sat Feb 13, 2010 10:07 pm; edited 2 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ባሻ ብሩ

ውሃ አጠጪ

Joined: 12 Feb 2005
Posts: 1368
Location: ዋርካ ቦተሊካ

PostPosted: Mon Feb 08, 2010 6:38 pm    Post subject: Reply with quote

Arrow እኔም እንደ ተድላ ! የቻላቸው ክፍል ወደላይ :: Smile
_________________
May God have mercy up on my enemies because I won't.
General George S. Patton
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 6:19 am    Post subject: Reply with quote

ባሻ ብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
Arrow እኔም እንደ ተድላ ! የቻላቸው ክፍል ወደላይ :: Smile
ተመስገን አምላኬ !!!!
ባሻ ነህ ? መቸም ጥሩ ሴት ዘውድ ናት ይባል የል :: ለሞኒካ ባልዋ ባትሆንም ሞኒካ በመልካም ቃላቶችዋ የደረቀውን ልብህን አልዝዛ ወደ ምግባረ ሰናይ በራፍ ሳታደርስህ አልቀረችም ሰሞኑን ባህሪህን ወደ ደግነት እየለወጥክ ነው :: ያለ ፍጥረቴ ያስለመድከኝን የስድብ ወልፍ ባንድ ድንጊያ ሁለት ወፍ እንዲሉ የልብህ ትርታ ሞኒካ ሁለታችንንም ሳትፈውሰን አልቀረችም ምክንያቱም ካልነካኸኝ አልነካህምና ካንተ ጋር ካልሆነ ከማን ጋር ዋርካ ስር አፍ ልካፈት ? :: ለማንኛውም በጀመርከው የባህሪ ለውጥ ያጽናህ !! መቸም ጠርጥር ነውና እንደሚባለው ጎርፍ ሲወስድ እያሳሳቀ ነውና የሞኒካን ነገር ግን አደራህን ባሹ እንዳትቆርጡባት !!!!!!!! መልካም ቀን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

ቻላቸው

ኮትኳች

Joined: 23 Nov 2009
Posts: 151
Location: politics

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 9:09 am    Post subject: Reply with quote

ቻላቸው እንደጻፈ(ች)ው:
Exclamation Exclamation ይጠንቀቁ Exclamation Exclamation የዝንብ ማጥፊያ የተረጨ አካባባቢ Exclamation Exclamation Exclamation ዝንቡ አንዳትገባ Exclamation Exclamation Exclamation
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post

Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2  Next
Page 1 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia