WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
ነገደ ጎበዜ
Goto page Previous  1, 2, 3, 4  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ቆቁ

ዋና አለቃ

Joined: 21 Sep 2003
Posts: 4564
Location: united states

PostPosted: Fri Feb 27, 2009 11:52 pm    Post subject: Reply with quote

እውነት ብርሀኑ የሻገተ ዲያስፖራ ነህ :
አንተም ሚስተር X የሻገተ ዲያስፖራ ነህ ::

እንዴት ይህንን ነገር ማገናዘብ ያቅታል እናንተ ወዳጆቼ Question

መጋቢት 14 1969 ማለት ማርች 6 1977 ገደማ ማለት ነው

ከማርች 1977 እስከ ዲሴምበር 1977 ማለት ደግሞ

ከመጋቢት 14 1969 እስከ ታህሳስ 1970 ማለት ነው

ከመጋቢት ጀምሮ እስከ ታህሳስ አካባቢ ድረስ ነው ኢሕአፓ ለዘላለም ይኑር : ነገደ ጎበዜ ይሰቀል ሲል የነበረ ወጣት እንዳልነበረ ይሆነው

ይህ አመተ ምህረት ነው የኢትዮጵያ ልጆች እንደ ጭዳ በነገደ ጎበዜ መሪነት እና በክፍሉ ታደሰ በል በለው ባይነት እንደ ጭዳ የታረዱት : ከታሪክ ማህደር እንደምንረዳው ::
ከዛ በሁዋላ የኢሕአፓ እስረኛ የመኤሶን እስረኛ እና የሌላውም በከርቸሌ የተደበላለቀበት ዘመን ነበር ይላል የታሪክ መረጃው ከሁሉም በኩል

ፈላስፋው ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በደዊ

አዲስ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 45
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 1:44 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ቆቁ Posted: Fri Feb 27, 2009 10:52 pm Post subject:

--------------------------------------------------------------------------------

እውነት ብርሀኑ የሻገተ ዲያስፖራ ነህ :
አንተም ሚስተር X የሻገተ ዲያስፖራ ነህ ::

እንዴት ይህንን ነገር ማገናዘብ ያቅታል እናንተ ወዳጆቼ

መጋቢት 14 1969 ማለት ማርች 6 1977 ገደማ ማለት ነው

ከማርች 1977 እስከ ዲሴምበር 1977 ማለት ደግሞ

ከመጋቢት 14 1969 እስከ ታህሳስ 1970 ማለት ነው

ከመጋቢት ጀምሮ እስከ ታህሳስ አካባቢ ድረስ ነው ኢሕአፓ ለዘላለም ይኑር : ነገደ ጎበዜ ይሰቀል ሲል የነበረ ወጣት እንዳልነበረ ይሆነውይህ አመተ ምህረት ነው የኢትዮጵያ ልጆች እንደ ጭዳ በነገደ ጎበዜ መሪነት እና በክፍሉ ታደሰ በል በለው ባይነት እንደ ጭዳ የታረዱት : ከታሪክ ማህደር እንደምንረዳው ::
ከዛ በሁዋላ የኢሕአፓ እስረኛ የመኤሶን እስረኛ እና የሌላውም በከርቸሌ የተደበላለቀበት ዘመን ነበር ይላል የታሪክ መረጃው ከሁሉም በኩል

የታሪክ መረጃው የሚለው / ነገደ ከአገር የወጣው
በሀምሌ /ነሀሴ 1969 ነው :: ታዲይ ቀይ ሽብሩን remote
መራው ልትሉን ነው :: ገና ብዙ ጉድ እንሰማልን ያስንበትን እንጂ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 2:50 am    Post subject: Reply with quote

በደዊ እንደጻፈ(ች)ው:

ሰውየው ምነው ምነው : በጊዜ አቆጣጠር ከነሐሴ 1969 .. በፊት የነበረው ጥር 1969 .. ነበር :: ጥር 26 ቀን 1969 .. "ነጭ ሽብር በቀይ ሽብር ይደመሠሣል :: አብዮታችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል !" የሚለውን የደርግን መግለጫ ያዘጋጁት እና በሬድዮና በቴሌቪዥን እንዲነበብ ያደረጉት ዶክተር ነገደ ጎበዜ ናቸው :: ያንን መግለጫ ተከትሎ በመላ ኢትዮጵያ የተከሠተውን እንኳን በዚያ የልጅ ዕድሜዬ ይቅርና አሁን 31 ዓመታት በኋላ ሣስበውም ይዘገንነኛል ::

ስለዚህ በዚያ አስከፊ የታሪክ ወቅት የነበሩ ሰዎች በሙሉ ሞተው ስላላለቁ ይህንን አገር ያወቀውን ጸሐይ የሞቀውን ሃቅ : ለመካድ ለምን አስፈለገ ?

ይህንን ሃቅ ራሣቸው ዶክተር ነገደ ጎበዜም አይክዱትም (ስለሌላ ዶክተር ነገደ ጎበዜ እያወራን ካልሆነ በስተቀር ):

ምን ዓይነት መድረቅ ነው Embarassed Embarassed Embarassed

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሚስተር -x

ውሃ አጠጪ

Joined: 02 Feb 2009
Posts: 1257

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 4:13 am    Post subject: Reply with quote

በመጀመሪያ ደረጃ ዲያስፖራ የሚባል ስድብ የለም :: The Ethiopian Diaspora (just like the Jewish diaspora) ማለት ከሀገሩ ውጪ የተበተነው ኢትዮጵያዊ ለማለት ብቻ ነው :: ያም ኬንያ , ሶማሊያ , ጅቡቲ , እስራኤል , አውሮፓ , ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ , አላስካ , ጃፓን , አንተንና እኔን , አንቺንም , ባለም ዙሪያ ያለዉን ሁሉ ያቅፋል ::

በሁለተኛ ደረጃ ሳትሳደቡ ሀሳብ ለማስተላለፍ ለምን ዪቸግራችሁዋል ? ለዚህ ቦታ አዲስ በመሆኔ ይሆናል አልገባ ያላችሁኝ ::

MR-X
_________________
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ …የማንየ ለትርስዐኒ። ወይጥጋዕ ልሳንየ ባጉርዔየ ለእሙ ኢተዘከርኩኪ!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በይሉል

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Sep 2004
Posts: 1115
Location: Beylul-60km North of Assab.

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 7:17 am    Post subject: Reply with quote

Quote:

በሌላ ምሳሌ ለመናገር --- ""መንግስቱ ሀይለማርያም ለኢትዮጵያ ምን የሚጨበጥ ታሪካዊ ቅን ስራ ሰራ ?"" ብለን ብንጠዪቅ ... ]ቆሻሻውን ለአንድ አፍታ ተወት አርገን .... መሀይምነትን ተዋጋ ... ብለን እንደ አንድ እውነታ ወይም (ሌጋሲ ) ማስረጃ መስጠት እንችላለን ::

MR-X

ባለፉት ሀያአመታት ግድም እንደዚህ አስቂኝ ነገር አጋጥሞኝ አያውቅም . አስቂኝነቱ ታሪክ ሲጨፈለቅ ስመለከት ዛሬ የመጀመርያየ ሆኖ ሳይሆን የተተፉ አምባገነኖች መልሰው ነፍስ ሲዘሩ እየገረመኝ ነው .

የመሰረተ ትምህርት ዘምቻው የገናናው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ተቀዳሚ ዋና አላማ ሆኖ ከአጼው ጀምሮ ሲታገሉለት የነበረ ቁዋሚ መርሀቸው ነበር .

መንግስቱ ሀይለማርያም የሶስተኛ ክፍለጦር ሰራዊትን ደሞዝ ለማስጨመር ከሀረር መጥቶ የቤተመንግስት ቀይ ወጥ ጣፍጦት በነነገደ ጎበዜ ሶሻሊስት ካድሬ ሆኖና በመጨረሻም ሰውበላ አምባገነን ሆኖ አገራሪሩን እንጥርጦስ ከትቶዋት የፈረጠጠ ቆሻሻ ወታደር ነው .

እና የመምህራንን ገድል ለደምመጣጩ ደርግ ማስረከብህ በጣም አስገርሞኛል .እዚህ መድረክ ምን አይነት ሰዎች እንዳሉም እንድጠራጠር አድርጎኛል .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ነቅንቄ

ኮትኳች

Joined: 01 Mar 2005
Posts: 244
Location: bet-amhara

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 7:50 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም

ይህን የተዥጎረጎረ ዘመን /ቀይ እና ነጭ / ከሚጠሉት አንዱ ነኝ . ነገርግን ድርጊቱን አሁን መለስ ብየ ስመለከተው ሁለት በጣም ጠቃሚ ነገሮች አበርክቶ ያለፈ ይመስለኛል .
1.የዉይይት እና ክርክር ባህል ከፍ ያለ ነበር . እንደዛሬው ስድብ እና ንዝንዝ አልነበረም .ትችት ....የሰላሂስ ...... ሎጂክ ..ታሪካዊና ሳይንሳዊ ክንዋኔዎች በውጣቱ ህይወት ዉስጥ ዋናዋናዎቹ ነበሩ .
2.ሁለተኛው ጠቃሚ ነገር ይህን ዉይይት እና ክርክር ባህላችን ሊያስተናግደው ባለመቻሉ ቀይ እና ነጭን ወልዶ ፍጅቱ ሁለተኛ አይደገምም የሚል ፍላጎት እና ቁጭትን ፈጥሮዋል .

ኢህአፓዎች አበራየማነአብን ለማስፈታት ግንባር ቀደም መሆናቸው / ነገደን እና ጉዋደኞቻቸዉን እንደሚያስፈነድቅ እርግጠኛ ነኝ . በሌላ በኩል ደግሞ ጌታቸው ሺበሺ ዶክተር ነገደን ""ሄደህ ሪፖርት በአስቸኩዋይ አምጣ "" ተብለው እንደአብዮት ጠባቂ ታዘው መሄዳቸው የሚያቅለሸልሽ ...የሚጎመዝዝ መራራ ጉዳይ ነው . ኤጭ ..ይሄ ደባሪ ቀይ ሽብር .....
_________________
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቆቁ

ዋና አለቃ

Joined: 21 Sep 2003
Posts: 4564
Location: united states

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 4:21 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሐይሉ የኔና የበደዊን ጽሁፍ አንድ ላይ ለምን አደባለቀኽው ?

በደዊ የታሪክ ማህደር የሚለው

በሐምሌ 12 1969 ማለትም በጁላይ 4 1977 ገደማ ኢማሌዲህ የተመሰረተበት እለት ነው ማለትም የኢሕአፓ መደምሰስ የተበሰረበት ማለት በሌላ ጎን

በሐምሌ 12 1969 ኢማሌዲህ ሲመሰረት መኤሶንን ወክለው የተሰለፉት ሐይሌ ፊዳ : ነገደ ጎበዜ እና ዳንኤል ታደሰ ነበሩ

ስለሆነም የቀይ ሽብሩ ወይም የመጀመሪያው አሰሳ ከተጀመረበት ከመጋቢት 14 እስከ ሐምሌ 12 1969 ድረስ አራት ወራት ናቸው ያለፉት በነዚህ አራት ወራቶች ነው የኢትዮጵያ ልጆች እንደ ጭዳ የረገፉት

እንደውም ሚያዚያ 22 - 23 1969 በተደረገው እልቂት ነው መላው የአዲስ አበባ ባንድ ሌሎት ጀምበር እንደ ጭዳ የረገፈው :

በዛን ጊዜ ነገደ ጎበዜ አዲስ አበባ ነበሩ

አንድ ያልገባኝ ነገር አለ ወዳጆቼ

1. እኚህ አለም እሸቴ ማናቸው ?
አንፌቃ እንደምትተባበረኝ ተስፋ አደርጋለሁ

2. ዲሞክራሲያ ይታተም የነበረው አዲስ አበባ ነበር ወይስ አሲምባ ?
ተድላ ሐይሉ እንደምትተባበረኝ ተስፋ አደርጋለሁ

3. የኢሕአፓ አንጃ የሚባለው ማለትም የብርሀነ መስቀል ረዳ እና የጌታቸው ማሩን ፈር የተከተለው አይደለም ወይ የተቀረውን የኢሕአፓ ቡድን ድምጥማጡን ያጠፋው ?

4. የክፍሉ ታደሰ ቡድን ኢማሌዲህ እስከሚመሰረት ድረስ አሁንም መኤሶንና ደርግ አባላት ላይ ማነጣጠሩን አቁሞ ነበር ወይ ?

5. ክፍሉ ታደሰ ለምን ተስፋዬ ደበሳይን ለማስመታት
ፈለገ ?

6. አዳነች ፍስሀዬ እና ነገደ ጎበዜ የተስፋዬ ደበሳየን አስከሬን ለማጣራት ነበር እዛ የተገኙት ይላል ጽሁፉ ምን ማለቱ ነው ይህ ጽሁፍ
አዳነች በክፍሉ ታደሰ በኩል ነገደ ጎበዜ በደርግ በኩል ምንድነው ነገሩ ?

7. ተስፋዬ ደበሳይን የሚፈልገው ሌላ ሐይል ነበር : ለምን ?

ፈላስፋው ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቆቁ

ዋና አለቃ

Joined: 21 Sep 2003
Posts: 4564
Location: united states

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 5:06 pm    Post subject: Reply with quote

ሚስተር -x እንደጻፈ(ች)ው:
በመጀመሪያ ደረጃ ዲያስፖራ የሚባል ስድብ የለም :: The Ethiopian Diaspora (just like the Jewish diaspora) ማለት ከሀገሩ ውጪ የተበተነው ኢትዮጵያዊ ለማለት ብቻ ነው :: ያም ኬንያ , ሶማሊያ , ጅቡቲ , እስራኤል , አውሮፓ , ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ , አላስካ , ጃፓን , አንተንና እኔን , አንቺንም , ባለም ዙሪያ ያለዉን ሁሉ ያቅፋል ::

በሁለተኛ ደረጃ ሳትሳደቡ ሀሳብ ለማስተላለፍ ለምን ዪቸግራችሁዋል ? ለዚህ ቦታ አዲስ በመሆኔ ይሆናል አልገባ ያላችሁኝ ::

MR-X

አትደንግጥ ሚስተር X ነቃ በል ወዳጄ

የአይሁዳውያን ዲያስፖራ እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በጣም የተለየ ነው

1. እንደ ቀልቤሳ ነገዎ የመሳሰሉትን ስለሚይዝ
2. አላማው ምን እንደሆነ ገና ያልተገለጠለት
3. ጠላቱ ማን እንደሆነ ያልተገለጠለት
4. እውነቱን መናገር የማይፈልግ
5. ሸውዶ ለመኖር የሚመኝ

እነዚህ ነጥቦች በአይሁዳውያን ዲያስፖራ ውስጥ አልነበሩም በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ግን እልፍ ነው ::

ፈላስፋው ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Feb 28, 2009 8:32 pm    Post subject: Reply with quote

ቆቁ እንደጻፈ(ች)ው:
ተድላ ሐይሉ የኔና የበደዊን ጽሁፍ አንድ ላይ ለምን አደባለቀኽው ?

አላደባለቅሁም :: መልሱም ለበደዊ ነው ::

Quote:
አንድ ያልገባኝ ነገር አለ ወዳጆቼ

1. እኚህ አለም እሸቴ ማናቸው ?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር እንደነበሩ አውቃለሁ ::
Quote:
2. ዲሞክራሲያ ይታተም የነበረው አዲስ አበባ ነበር ወይስ አሲምባ ?
ተድላ ሐይሉ እንደምትተባበረኝ ተስፋ አደርጋለሁ

በእውነቱ አላውቅም :: በወቅቱም ያንን ለማወቅ የሚያስችለኝ ዕድሜ ላይ አልነበርኩም ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በደዊ

አዲስ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 45
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Mar 02, 2009 12:19 am    Post subject: ግርማ ከበደ Reply with quote

ቆቁ እንደጻፈ ():
Quote:

ተድላ ሐይሉ የኔና የበደዊን ጽሁፍ አንድ ላይ ለምን አደባለቀኽው ?

በደዊ የታሪክ ማህደር የሚለው

በሐምሌ 12 1969 ማለትም በጁላይ 4 1977 ገደማ ኢማሌዲህ የተመሰረተበት እለት ነው ማለትም የኢሕአፓ መደምሰስ የተበሰረበት ማለት በሌላ ጎን

በሐምሌ 12 1969 ኢማሌዲህ ሲመሰረት መኤሶንን ወክለው የተሰለፉት ሐይሌ ፊዳ : ነገደ ጎበዜ እና ዳንኤል ታደሰ ነበሩ

ስለሆነም የቀይ ሽብሩ ወይም የመጀመሪያው አሰሳ ከተጀመረበት ከመጋቢት 14 እስከ ሐምሌ 12 1969 ድረስ አራት ወራት ናቸው ያለፉት በነዚህ አራት ወራቶች ነው የኢትዮጵያ ልጆች እንደ ጭዳ የረገፉት

እንደውም ሚያዚያ 22 - 23 1969 በተደረገው እልቂት ነው መላው የአዲስ አበባ ባንድ ሌሎት ጀምበር እንደ ጭዳ የረገፈው :

በዛን ጊዜ ነገደ ጎበዜ አዲስ አበባ ነበሩ
የኔን ድግሞ ስማኝ

ትድላ
Quote:

ሰውየው ምነው ምነው : በጊዜ አቆጣጠር ከነሐሴ 1969 . . በፊት የነበረው ጥር 1969 . . ነበር :: ጥር 26 ቀን 1969 . . "ነጭ ሽብር በቀይ ሽብር ይደመሠሣል :: አብዮታችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል

ይህ ትክክል ነው ::ነግር ግን ሆን ተብሎ የምይጠቅስ ነገር አለ ::ይህውም ይህን የምንግስቱን አባባል በመከተል በጥር ማለቂያ ላይ ይሁን በይካቲት ላይ ግርማ ከበደ የሚባል
የቀበሌ ሊቀ መንበር :: ከብርሀነ ሰላም ማተሚያ ቤት ስወች
አውጥቶ ይረሽናል :: በምግስቱ ደርግ ይህንን ሰው ያወጣና
በአደባባይ firing sqad ከሌሎች የቀበሌ ዘበኞች ጋር
ይረሽነዋል :: ከዚያች ቀን ጀምሮ በድርግና በመኢሶን መሀክል ትብብር አልንበርም :: ተከታዩ 5 ወር ድርግና ውዝ ሊግ ባንድ ወገን EPRP በሌላ ወገን ሆነው መኢሶንን የፈጁበት ወራቶች ነበር :: በኔ ግምት ብዚይን ግዜ በደርግ የተገደለው የመኤሶን ስው EPRP ከገደለው ሳይበዛ አይቀርም :: በዚያን ወቅት መኢሶን ብቻ አልነበረም የመንግስቱ ሰለባ የሆኑት :: አገር ውዳዱ ኮሎነል አጥናፉ አባተ : የማልሬድ መሪወች ሌሎች የሚጠቅሱ ናችው ::

ታድያ ለኔ የሚክብዴኝ ነገር : የራሱን አባሎች ከደርግ ለመጠብቅ ያልቻለን ድርጅት ቀይ ሽብርን በማህንዲስንት መርው የሚለው አባባል ነው ::

ወንድሞቼ : ይህ ወቅት የሱማሌ ውረራ ይተፈጸመበት
ሶቬት በአገራችን : ጣልቃ የገቡበት :: እነ አምሳ አልቃ ለገሰ የአብዮቱ ውና መሪ የሆኑበት ወራት መሆኑን አትርሱ :: በሚሶንና በደርግ መሀል በዚህ ወቅት ከባድ ልዩነት ነበር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በደዊ

አዲስ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 45
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Mar 02, 2009 12:36 am    Post subject: ግርማ ከበደ Reply with quote

ቆቁ እንደጻፈ ():
Quote:

ተድላ ሐይሉ የኔና የበደዊን ጽሁፍ አንድ ላይ ለምን አደባለቀኽው ?

በደዊ የታሪክ ማህደር የሚለው

በሐምሌ 12 1969 ማለትም በጁላይ 4 1977 ገደማ ኢማሌዲህ የተመሰረተበት እለት ነው ማለትም የኢሕአፓ መደምሰስ የተበሰረበት ማለት በሌላ ጎን

በሐምሌ 12 1969 ኢማሌዲህ ሲመሰረት መኤሶንን ወክለው የተሰለፉት ሐይሌ ፊዳ : ነገደ ጎበዜ እና ዳንኤል ታደሰ ነበሩ

ስለሆነም የቀይ ሽብሩ ወይም የመጀመሪያው አሰሳ ከተጀመረበት ከመጋቢት 14 እስከ ሐምሌ 12 1969 ድረስ አራት ወራት ናቸው ያለፉት በነዚህ አራት ወራቶች ነው የኢትዮጵያ ልጆች እንደ ጭዳ የረገፉት

እንደውም ሚያዚያ 22 - 23 1969 በተደረገው እልቂት ነው መላው የአዲስ አበባ ባንድ ሌሎት ጀምበር እንደ ጭዳ የረገፈው :

በዛን ጊዜ ነገደ ጎበዜ አዲስ አበባ ነበሩየኔን ድግሞ ስማኝ
ትድላ
Quote:
Quote:

ሰውየው ምነው ምነው : በጊዜ አቆጣጠር ከነሐሴ 1969 . . በፊት የነበረው ጥር 1969 . . ነበር :: ጥር 26 ቀን 1969 . . "ነጭ ሽብር በቀይ ሽብር ይደመሠሣል :: አብዮታችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯልይህ ትክክል ነው ::ነግር ግን ሆን ተብሎ የምይጠቅስ ነገር አለ ::ይህውም ይህን የምንግስቱን አባባል በመከተል በጥር ማለቂያ ላይ ይሁን በይካቲት ላይ ግርማ ከበደ የሚባል
የቀበሌ ሊቀ መንበር :: ከብርሀነ ሰላም ማተሚያ ቤት ስወች
አውጥቶ ይረሽናል :: በምግስቱ ደርግ ይህንን ሰው ያወጣና
በአደባባይ firing sqad ከሌሎች የቀበሌ ዘበኞች ጋር
ይረሽነዋል :: ከዚያች ቀን ጀምሮ በድርግና በመኢሶን መሀከል ትብብር አልንበርም :: ትከታዩ 5 ወር ድርግና ውዝ ሊግ ባንድ ወገን
EPRP በሌላ ወገን ሆነው መኢሶንን የፈጁበት ወራቶች ነበር :: በኔ ግምት ብዚይን ግዜ በደርግ የተገደለው የመኤሶን ስው EPRP ክገደለው ሳይበዛ አይቀርም :: በዚያን ወቅት መኢሶን ብቻ አልነበረም የመንግስቱ ሰለባ የሆኑት :: አገር ውዳዱ ኮሎነል አጥናፉ አባተ : የማልሬድ መሪወች ሌሎች የሚጠቅሱ ናችው ::

ታድያ ለኔ የሚከብደኝ ነገር : የራሱን አባሎች ከደርግ ለመጠብቅ ያልቻለን ድርጅት ቀይ ሽብርን በማህንዲስንት መርው የሚለ አባባል ነው ::

ወንድሞቼ : ይህ ወቅት የሱማሌ ውረራ ይተፈጸመበት
ሶቬት በአገራችን : ጣልቃ የገቡበት :: እነ አምሳ አልቃ ለገሰ የአብዮቱ መሪና የቲወሪ ተንታኝ የሆኑበት ወራት መሆኑን አትርሱ :: በሚሶንና በደርግ መሀል በዚህ ወቅት ከባድ ልዩነት ነበር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሚስተር -x

ውሃ አጠጪ

Joined: 02 Feb 2009
Posts: 1257

PostPosted: Mon Mar 02, 2009 2:01 am    Post subject: Reply with quote

በደዊ

ተስፋዬ መኮንን (ከማሌሪድ ጎራ ) ""ይድረስ ለባለታሪኩ "" በሚል ርእስ የጻፈውን መጽሀፍ የማንበብ እድል አጋጥሞሀል ? እንብበህው ከሆነ በመኢሶን /በነገደ ላይ ስለሰጠው ዉስጣዊ ግንዛቤ ምን ትላለህ :: ምናልባት ዪሄ ወደ ሰብሰብ ያለ ውይይት ይመራን ይሆናል ::

MR-X
_________________
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ …የማንየ ለትርስዐኒ። ወይጥጋዕ ልሳንየ ባጉርዔየ ለእሙ ኢተዘከርኩኪ!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወዲ ማየጃህጃህ

መንገደኛ

Joined: 02 Mar 2009
Posts: 2

PostPosted: Mon Mar 02, 2009 5:41 am    Post subject: Re: BRUKYIRGA! Reply with quote

ሰሙን ስሰማ ይሰቀጥጠኛል ! ውይ !

ወርቅሰው 1 እንደጻፈ(ች)ው:
BRUKYIA!
ትክክል ነው አቀራረብህ :: እኔም ያንኑ የመሰለ ሁኔታውን የሚያመለክት ነበር የሰማሁት :: ተጨማሪ ቢኖር የሰሜን የመን ሶሻሊስቶችም በነገደ ጎበዜ ግልግል መሐል ገብተው እንደነበረ ነው የሚታወቀው :: ብቻ ሚኤሶኖች እንደማንኛቸው ፖለቲካ ድርጅቶች ጉዳት በኢትዮጵያ ላይ እንዲደርስባት አድርገዋል :: በወቅቱ በጭካኔ የሚወዳደራቸው የለም ነበር :: ካድሬዎቻችው ደግሞ ሽጉጥ ደብቀው በመያዝ በኃላ ሲሰክሩ እሱን ያወጡና ህዝብን በተለይም ወጣቱን ትውልድ ያስፈራሩበት ነበር :: "አስታጥቁን አታስጨርሱን " እያሉ የህዝብ ድርጅትን ይዘው በህዝባችን ላይ ይፈርዱ ነበረ :: እነኛ ሁሉ ሊታሰቡ ይገባል ?

ለማንኛውም አቀራረብህ ትክክለኛ ስለነበር የኔንም አስተሳሰብ አስጨመርከኝ ::

ወርቅሰው 1
(ሰሐሊን )
BRUKYIRGA እንደጻፈ(ች)ው:
በደርግ ጊዜ የወዝ ሊግ መስራች የነበረ ከዶ / ሰናይ ልኬ ጋር የቀረበ ትስስር የነበረው
ደርግ በውስጡ የሰረጉትን የኢህአፓ አባላት (ሻምበል ሞገስ /ሚካኤል ሻለቃ ሲሳይ ሀብቴ .......)ሲረሸኑ ለህዝብ የሚነበበውን ጽሁፍ ያዘጋጀ
/ ሰናይ ልኬ (አለቃው )በኮ /ዳንኤል አስፋው (የደርግ የጸጥታ ሀላፊ )ምክትል ሲገደል ወዝሊግ በመዳከሙ ከደርግ ጉያ ያፈተለከ
ከኩባው ፊደል ካስትሮ ጋር ቅርበት የነበረው በዚህም በመንግስቱ /ማርያም ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማድረግ ወደ . (በቦሌ ) ሾልኮ ሲገባ በደርግ መረጃዎች ቢያዝም በኩባ መግስት ልመና በመጣበት ቢመለስም በኩባና በደርግ መሀከል የነበረው ግንኙነት ላይ ጥቁር የጣለ ከፍተኛ የሥልጣን ጥማት ያለበት መሆኑ ይታወቃል
ለማጠቃለል በደርግ ጊዜው እልቂት ትልቅ ተሳትፎ የነበረው ሰው ነው በዚህ አጋጣሚ ኢሀፓ ከተባለው ድርጅትም ባልተናነሰ ለእልቂቱ ትልቅ አስተዋጾ አድርጎል በመጨረሻም ይህንን ሰውዬ ፍሩት !!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅሰው 1

ዋና አለቃ

Joined: 05 Nov 2003
Posts: 3350
Location: Sehalin

PostPosted: Mon Mar 02, 2009 1:23 pm    Post subject: Re: BRUKYIRGA! Reply with quote

[color=blue]ወዲ ወይም ጓል ማየጃጃህጃህ !
ልክ ነው ስማቸው ያስፈራል በኢትዮጵያ ላይ መተውባት የነበሩት ሁሉ :: እስከዛሬም ድረስ :: ግን ጊዜ ጥሩነው የሁሉንም ሀሳብ እየነጠረ ስለሚመጣ ለወደፊቱ ጥሩ ዲሞክራሲያዊን አስተሳሰቦች ይኖራሉ ይመጣሉ በሚል እመኛለሁ :: ያለፈው እርግጥ ነው እጅግም ያስፈሩ ነበሩ ::

ሌላው @ጸሐይቱ ባራኺን ታውቃታለህ /? ማይጃህጃህን አውቃታለሁ :: ታዲያ የጸሐይቱ ባራኺን ዘፈን በመስማት ነበር ሄደን ያየናት ::

ጸሐይቱ ስትዘፍን ሁሉንም አልቺለውም ግን የምትለው በሚገባ ስለምን እንደሆነ የረዳኝ ነበር ::

ሃማ ግደይ ደብዳቤ መጹኡኒ : ደስ ይበልካ ሃወሆይ ደስይሉኒ :: ደብዳቤ መጣልኝ ደስ ይበልህ ደስ ብሎኛል :: እንደማለት ይመስለኛል :: ከዚያ ሸጋ ድምጿ ጋር :: ያን ጊዜ ነው ተሰብስበን ማይጃህጃህን የጠየቅናት ::

ጸሐይቱ ባራኪንና ትበርህ ተስፋ ሁነኝ በተለይ ትበርህን አሰብ በነበረቺበት ጊዜ የጥቁር አባይ ባለቤት ሆና በሚገባ አውርቼአታለሁ :: ከዘፈኗም በልመና ትንሽ ገረፍ ገረፍ ታደርግ ነበር :: በዚያን ጊዜ ጥሩ ሰዓት ነበር :: ህዝብ እርስበርሱ የፈለገው ችግር ይኑር ይስማማና አብሮም ይሰለፍ ነበር ለሁሉም ::'

ነገሩ የተበላሸው ደርግ ከመጣ በኃላ ነበር :: ኢትዮጵያ በምንም ዓይነት ሮቮሎሺኖች የሚካሄዱባት አገር አይደልöእችም አትመስልምም :: ህዝቧ የኖረው በነጻና በነጻነት ውስጥ ነበር :: ቢያንስ እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ የህሊና ነጻነቶች ነበሩት ::

ደርጉ ሲመጣ እነኝህ የተባሉት ፓርቲዎች እየተግተለተሉ ከነ መጫኛቸውና መጫኛቸውም ያልጠበቅ እርስበርሱ የሚማታና የሚወዛወዝ ስለነበረ እራሳቸውም ጠፍተው አሪቱንም አጠፏት ህወሀት የጀመረውና ዛሬ እየዳከረበት የሚገኘው ምክንያት ዱሮ ነበር የተጀመረው :: ነገር ግን ከዚያ ካሳለፍነው ተምረናል ወይ በሚል ያስባሉን ? ወይስ እንደጥንቱ አሁንም ለግድያና ለፍጅት እያሰሉ ነው ?

ነገ ህወኃት ቢደረመስ ማነውንና ማን ሆነው ይሆን ኢትዮጵያ በህጋዊ ደረጃ ጠብቀውና አስጠብቀው አመራሮችን በጉልህ የሚሰጡ ? እነኛ ሁሉ ጥያቄዎች ናቸው :: እነኛን ግን ዘወር ለው አያዩዋቸውም :: ምክንያቱም ? የራሳቸውን ፍላጎትና የራሳቸውንም ትርጉም ይዘው ስለሚጓዙና በዚያም ዓይነት ስለኖሩ ለሌሎች እስከዚህ ቅድሚያ የማይሰጡ ናቸው ::

ሃሜታና ማግለል ግን ያውቁበታል :: ያባይሆን ኖሮ እስካሁን ይታደጋል እንጅ ሰው እንዴት ቁልቁል ልክ እንደካሮት ያድጋል ? በነኛ ምክንያት ሚኤሶንም ሆነ ኢሕ አፓ : ኦነግም ሆነ ህወሀት : ወያኔ # ሆነ ገለመሌ ሁሉም የአንድ ቦርሳ ትውልድና ሰዎች ናቸው :: አይታረሙም :: መከፋፈልን ሲያውቁበት ላሳር ነው ደግሞ :: እነኛ ሳይስተካከሉ አመራር ላይ ቢመጡ ለህዝቡም ለአገሪቱም አስቸጋሪ ይሆናል ?

አንድ ቁምነገር ተናግሬ ላብቃስቲ !!! በአገራችን አንድም ነጻ ውጭ የሚባል የለም ነበር :: ታዲያ ታሪኩን አንድ ትልቅ ሰው ያኔ በልጅነቴ ሲነግሩኝ እንዲህ ይላሉ !

የሐረር ሰው ናቸው ያውም የአደሬ ሽማግሌ :: ልጄ አሉኝ እኛ ነበርን የመን ድረስ ግብጽ ድረስ ተጉዘን የመጀመሪያ ስደተኞች የነበረነው አሉኝ :: ለምን ብላቸው አስደሬን ነጻነቷን እንድታገኝ ስንጠይቅላት ነበር :: እንዴ ሰውዬው አብደዋል ይሆን ወይስ ጫት ዛሬ ወደከተማ አልመጣስ ይሆን ስለአልቃሙ ነው የሚያዘባርቃቸው በሚል ታዝቤ ልሄድ ስነሳ ::

እየሳቁ ቁጭ በል ልጄ እኔ አላበድኩም የምነግርህ ታሪክን ነውና አስተውለህ ጊዜ ሲኖርህ ጊዜውም ሲቃናልህ ለመሳዮጭ ትነግራቸዋለሁ ትምህርት ነው በሚል መከሩኝ ከዚያ የመን አደን ውስጥ እንዴት ይኖሩ እንደነበረ :. ካይሮ ግብጽ ደግሞ አልዛር ዩኒቨርስቲ ከአገራቸው በአንደኛ ደረጃ በማለፋችወው እዚያ የተማሩ መሆናቸውን በዚያሰዓት አደሬን ነጻ ለማውጣት የመጀመሪያው ሮቮሎሺነሪ ኃይል ይመሩ እንደነበረ ጭምር ከሳቸው በፊት አንድም ነጻነት ግንባር ሆነ ፓርቲ እንደሌለ ጭምር አስረዱኝ ከዚያ በኅላ ነበር ይሄሁሉ ስምና ወሬ የተበሳበሰብን በሚል አስረዱ :: ሽማግሌው በዚህ ሰዓት የሚኖሩ አይመስለኝም :: ዘመኑ 40 ዓመት በላይ ነው በዚያን ወቅት አርጅተው ነበር ::

ይህን ካልኩ አደሬዎች ታሪኩንና ታሪካቸውን ስለሚረዱ እነሱ ቢያስረዱን ይመረጣል እላለሁ :: ሚኤሶንም ሆነ ሌሎቹ ኢትዮጵያን እና የህዝቧንም ፍላጎቶች ምኞቶች ሳይረዱ ሳያውቁ በርሊን ላይ ያደረጉት ስብሰባ ሊያስማማቸው እንዳልቻለ ሁሉ ያን አገር ልጆች ወንድምና አማቾች ተላለቁ ለምን ? እነኛ ሁሉ ስህተቶችና እና እኛ እናውቅለታለን ህዝቡ ምንም የሚያውቀው የለም በሚል በመገመታቸው ነበር :: ነገር ግን ህዝብን መናቅ ነውር ነው :: አሁንም ድረስ ህወሀት ህዝቡ የመረጣቸው ተመራጮች ሰብስቦ አስሮና ገድሎ ከአገርም እንዲወጡ ስደተኛ አድርጎአቸው ይሄው እየኖረ ነው :: አላፈረም ይሳደባልም :: ፕሮፓጋንዳዎችንም ይነዛባቸዋል :: ነገር ግን ህዝቡ መርጧቸው እንደነበረ አሁን ረስቷል ? እነኝህ የመሰሉ ስህተቶች በሁሉም ፓርቲዎች በኩል ይፈጸሙ ነበር :: አሁን የሚያስፈልገው ያን መሳይ እዳይደገም ነው ::

አዲስ አበባን ያሸነፈው ሌላ ፓርቲ አሁን የሚመራት ግን ህወሀት ? ራሱን የቻለ ወንጀልኝነት ይመስላል :: ታዲያ ምን ሲደረግ ነው ዲሞክራሲ እየተባለ በኢትዮጵያ የሚሰበከው ? ዲሞክራሲ የሚባል አንድም ቦታ የለም በምድረ ኢትዮጵያ ? ዲሞክራሲ ያለበት አገር ኦጋዴን የመሰለ የኑሮውና የህዝቡንም ቀልብ ያሟጠጠ አስፈሪ ሁኔታዎች የሚታዩኢበት አይመስሉም አይሆኑምም :: እነኛ ሁሉ ምክንያቶች ናቸው :: የተለየ አስተሳሰብ የያዙ ቡድኖችችም ሆኑ ቤርተሰቦች ሰዎችን በሌሊት ተሄዶ የሚታፈኑበት አገር ቢኖር ኢትዮጵያ ነች :: ታዲያ ያዲሞክራሲ ይባላል ወይስ የሽፍቶች አምባ ?

ወቅሰው 1
(ሰሐሊን )/color]

ወዲ ማየጃህጃህ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰሙን ስሰማ ይሰቀጥጠኛል ! ውይ !

ወርቅሰው 1 እንደጻፈ(ች)ው:
BRUKYIA!
ትክክል ነው አቀራረብህ :: እኔም ያንኑ የመሰለ ሁኔታውን የሚያመለክት ነበር የሰማሁት :: ተጨማሪ ቢኖር የሰሜን የመን ሶሻሊስቶችም በነገደ ጎበዜ ግልግል መሐል ገብተው እንደነበረ ነው የሚታወቀው :: ብቻ ሚኤሶኖች እንደማንኛቸው ፖለቲካ ድርጅቶች ጉዳት በኢትዮጵያ ላይ እንዲደርስባት አድርገዋል :: በወቅቱ በጭካኔ የሚወዳደራቸው የለም ነበር :: ካድሬዎቻችው ደግሞ ሽጉጥ ደብቀው በመያዝ በኃላ ሲሰክሩ እሱን ያወጡና ህዝብን በተለይም ወጣቱን ትውልድ ያስፈራሩበት ነበር :: "አስታጥቁን አታስጨርሱን " እያሉ የህዝብ ድርጅትን ይዘው በህዝባችን ላይ ይፈርዱ ነበረ :: እነኛ ሁሉ ሊታሰቡ ይገባል ?

ለማንኛውም አቀራረብህ ትክክለኛ ስለነበር የኔንም አስተሳሰብ አስጨመርከኝ ::

ወርቅሰው 1
(ሰሐሊን )
BRUKYIRGA እንደጻፈ(ች)ው:
በደርግ ጊዜ የወዝ ሊግ መስራች የነበረ ከዶ / ሰናይ ልኬ ጋር የቀረበ ትስስር የነበረው
ደርግ በውስጡ የሰረጉትን የኢህአፓ አባላት (ሻምበል ሞገስ /ሚካኤል ሻለቃ ሲሳይ ሀብቴ .......)ሲረሸኑ ለህዝብ የሚነበበውን ጽሁፍ ያዘጋጀ
/ ሰናይ ልኬ (አለቃው )በኮ /ዳንኤል አስፋው (የደርግ የጸጥታ ሀላፊ )ምክትል ሲገደል ወዝሊግ በመዳከሙ ከደርግ ጉያ ያፈተለከ
ከኩባው ፊደል ካስትሮ ጋር ቅርበት የነበረው በዚህም በመንግስቱ /ማርያም ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማድረግ ወደ . (በቦሌ ) ሾልኮ ሲገባ በደርግ መረጃዎች ቢያዝም በኩባ መግስት ልመና በመጣበት ቢመለስም በኩባና በደርግ መሀከል የነበረው ግንኙነት ላይ ጥቁር የጣለ ከፍተኛ የሥልጣን ጥማት ያለበት መሆኑ ይታወቃል
ለማጠቃለል በደርግ ጊዜው እልቂት ትልቅ ተሳትፎ የነበረው ሰው ነው በዚህ አጋጣሚ ኢሀፓ ከተባለው ድርጅትም ባልተናነሰ ለእልቂቱ ትልቅ አስተዋጾ አድርጎል በመጨረሻም ይህንን ሰውዬ ፍሩት !!!!!!

_________________
ለሁሉም ጊዜ አለው:: ለደስታም ሆነ ለሃዘን የሰውልጅ ሆይ አንተ ማነህ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Mar 02, 2009 8:22 pm    Post subject: Re: ግርማ ከበደ Reply with quote

በደዊ እንደጻፈ(ች)ው:
የኔን ድግሞ ስማኝ
ትድላ
Quote:
Quote:

ሰውየው ምነው ምነው : በጊዜ አቆጣጠር ከነሐሴ 1969 . . በፊት የነበረው ጥር 1969 . . ነበር :: ጥር 26 ቀን 1969 . . "ነጭ ሽብር በቀይ ሽብር ይደመሠሣል :: አብዮታችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯልይህ ትክክል ነው ::ነግር ግን ሆን ተብሎ የምይጠቅስ ነገር አለ ::ይህውም ይህን የምንግስቱን አባባል በመከተል በጥር ማለቂያ ላይ ይሁን በይካቲት ላይ ግርማ ከበደ የሚባል
የቀበሌ ሊቀ መንበር :: ከብርሀነ ሰላም ማተሚያ ቤት ስወች
አውጥቶ ይረሽናል :: በምግስቱ ደርግ ይህንን ሰው ያወጣና
በአደባባይ firing sqad ከሌሎች የቀበሌ ዘበኞች ጋር
ይረሽነዋል :: ከዚያች ቀን ጀምሮ በድርግና በመኢሶን መሀከል ትብብር አልንበርም :: ትከታዩ 5 ወር ድርግና ውዝ ሊግ ባንድ ወገን
EPRP በሌላ ወገን ሆነው መኢሶንን የፈጁበት ወራቶች ነበር :: በኔ ግምት ብዚይን ግዜ በደርግ የተገደለው የመኤሶን ስው EPRP ክገደለው ሳይበዛ አይቀርም :: በዚያን ወቅት መኢሶን ብቻ አልነበረም የመንግስቱ ሰለባ የሆኑት :: አገር ውዳዱ ኮሎነል አጥናፉ አባተ : የማልሬድ መሪወች ሌሎች የሚጠቅሱ ናችው ::

ታድያ ለኔ የሚከብደኝ ነገር : የራሱን አባሎች ከደርግ ለመጠብቅ ያልቻለን ድርጅት ቀይ ሽብርን በማህንዲስንት መርው የሚለ አባባል ነው ::

ወንድሞቼ : ይህ ወቅት የሱማሌ ውረራ ይተፈጸመበት
ሶቬት በአገራችን : ጣልቃ የገቡበት :: እነ አምሳ አልቃ ለገሰ የአብዮቱ መሪና የቲወሪ ተንታኝ የሆኑበት ወራት መሆኑን አትርሱ :: በሚሶንና በደርግ መሀል በዚህ ወቅት ከባድ ልዩነት ነበር ::

በደዊ :- የቀኖቹ ቅደም ተከተል ተምታቶብሃል :: ነገሩን በቅንነት እስከተመለከትከው ድረስ አሁንም የምናውቀውን ከማቅረብ ወደ ኋላ አንልም ::

ስለ ነፈሰ -በላው ግርማ ከበደ አገዳደል :
ግርማ ከበደ በራሱ ሰዎች ለመበላት የበቃው በመኢሶንነቱ ሣይሆን የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን አጎት 'ዶክተር አሥራት ወልዴን ' ከትምህርት ሚኒስቴር ወስዶ ለመረሸን ሲዘጋጅ ወሬው ለቤተሰብ ተነግሮ : የራሳቸው የኮሎኔል መንግሥቱ ልጅ አንድነት መንግሥቱ ለአባቱ ሥብሰባ ቦታ ድረስ ሄዶ አስደንጋጩን ዜና በመንገሩ ወዲያውኑ ግርማ ከበደ በቁጥጥር ሥር እንዲውልና አስፈላጊ የኋላ ታርጋ (ወንጀል ) ተለጥፎለት ነው የተረሸነው :: በኋላም 1983 .. አገዛዛቸው ዕድሜው አጭር እንደሆነ ሲገነዘቡ ኮሎኔል መንግሥቱ ከአገር ከመፈርጠጣቸው በፊት ዶክተር አሥራት ወልዴን በዙምባብዌ የኢትዮጵያ አምባሣደር አድርገው ላኳቸው :: አሁንም ዶክተር አሥራት ወልዴ እዚያው ዚምባብዌ ይኖራሉ :: ስለዚህ የግርማ ከበደ አገዳደል የቤተሰብን ደህነነት ከማስጠበቅ አኳያ ኮሎኔል መንግሥቱ የወሰዱት እርምጃ እንጂ ከመኢሶን ጋር በነበራቸው የፖለቲካ ልዩነት አልነበረም :: በእርግጥ በመኢሶን ሰዎች አካባቢ እንደዚያ ይታሠብ ከነበረ ማሥረጃውን ብታቀርብልን መልካም ይሆናል :: አንተ በደርግና በመኢሶን መካከል እያልክ ገልጸኸዋል :: እኔ ደግሞ በአብዮታዊ ሰደድና በመኢሶን መካከል ማለቱን እመርጣለሁ :: ምክንያቱም ደርግ ከፊውዳል እስከ አክራሪ ማርክሲስት -ሌኒኒስት አሥተሣሰብ ያላቸውን ወታደሮች ያቀፈ ሥብሥብ ነበርና Exclamation

ስለ ወዝሊግ እና አብዮታዊ ሰደድ ግንኙነት :-
ወዝሊግም አብዮታዊ ሰደድም የተመሠረቱት በዶክተር ሰናይ ልኬ ነበር :: በአመሠራረት ወዝሊግ ይቀድማል :: ዶክተር ሰናይ ልኬ ለምን ሁለት ድርጅቶች እንደመሠረቱ ምክንያቱን የሚያውቁት እርሣቸው ብቻ ናቸው :: ነገር ግን እድሜ ለቆራጡ ለመቶ አለቃ ዮሐንስ ምትኩ እኒያን ነፈሰ -በላ አረመኔ ሰው ሕይወቱን ሰውቶ ገላግሎናል :: (ኮሌኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምንም ገላግሎን ቢሆን ኖሮ እንዲህ የሻቢያና የወያኔ መጫዎቻ አንሆንም ነበር :: ) ነገር ግን ዶክተር ሰናይ ልኬ ወዝሊግን ሲመሠርቱ በአብዛኛው ከአየር ኃይል ባልደረቦች በተመለመሉ አባሎች ነበር የሞሉት (ሻምበል ፍቅረ ሥላሤ ወግደረስን ይጨምራል ) :: አብዮታዊ ሰደድን ደግሞ ከኮሎኔል መንግሥቱ ጋር በመመካከር የመሠረቱት ድርጅት ሲሆን በአብዛኛው የጦር ሠራዊቱ አባላትን ያቀፈ ነበር :: ስለዚህ ዓላማቸው ምናልባት በጦሩ ድጋፍ ኮሎኔል መንግሥቱን አስወግደው 'ኢትዮጵያ ፍጹም ፈላጭ ቆራጭ ገዢ " ለመሆንም ይሆናል :: ይህን ደግሞ የሚያውቋቸው ሰዎች የጻፏቸውን በማገናዘብ ማረጋገጥ ይቻላል ::

ስለ ኮሎኔል አጥናፉ ያቀረብከው አገላለጽ ትክክል ነው :: እርሣቸውም ከቀይ ሽብር ሰለባዎች አንዱ ነበሩ :: አሟሟታቸውም የኮሎኔል መንግሥቱን አገዛዝ መሠሪነት የሚያንጸባርቅ እና ኢትዮጵያንም ወደባሠ የእርስ -በእርስ የደም መፋሠሥ እንድታመራ ያደረገ ነበር ::

በተረፈ 'ሚስተር x' እንደ መከረህ የአቶ ተስፋዬ መኮንን - 'ይድረስ ለባለ ታሪኩ ' የሚለውን መጽሐፋቸውን ፈልገህ ብታነብ ምናልባት ብዙዎቹ ነገሮች ግልጽ ሊሆኑልህ ይችላሉ ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4  Next
Page 3 of 4

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia