ሰበር ዜና -አንዳርጋቸው ጽጌ ከቃሊቲ ማረሚያ ወጥቷል

ሰበር ዜና -አንዳርጋቸው ጽጌ ከቃሊቲ ማረሚያ ወጥቷል

andargachew tsige
andargachew tsige

የቦሌ መንገድ በመኪና ጥሩንባ ጩኽት ደምቃለች!

አንዲ ወደቤቱ እየመጣ ነው!

በኢትዮጵያ የኢንግሊዝ ኤምባሲ መኪናዎች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በር ጠብቀው ወስደውታል።

የአንዳርጋቸዉ ጽጌ እህት ወ/ሮ ኑኑ ጽጌ ጨምሮ ከተለያየ ቦታ የመጡ የአዲስ በበባ ወጣቶች ተቀብለውታል::

የጉዞዉ ሰነድ በማለቁ ዛሬ ወደ ቤተሰቦቹ፤ አገረ እንግሊዝ ይጓዛል ~ ተብሏል

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ቤት በርካታ ወጣቶች ተሰብሰበው እየጠበቁት ነው።

ወላጆቹም፤ እንዲህ ተውበው የልጃቸውን መምጣት እየጠበቁ ናቸው።

እንግሊዙ ስካይ ኒውስ Sky News ዘገባ ከሆነ አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ፤ ሰኞ ማታ ለንደን ይገባሉ።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ትናንት እሁድ ምሳ ሰዓት አካባቢ ለአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወይዘሮ የምሥራች ኃ/ማርያም ስልክ በመደወልአንዳርጋቸው በይቅርታ ከእስር ተፈተው በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ለንደን እንደሚደርሱ አረጋግጠውላቸዋል።

ልጆቹም የአባታቸውን አይን ለማየት በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።

ጌጡ ተመስገን