ኢትዮጵያ በለውጥ ጉዞ፤ ከአንባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዲሞክራሲ

ኢትዮጵያ በለውጥ ጉዞ፤ ከአንባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዲሞክራሲ

ለውጡየሰነቃቸውተስፋዎች፣የተወሰዱበጎእርምጃዎችእናያንጃበቡአደጋዎች ድልድይ፤በአውሮፓየኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያዊያንየውይይትመድረክ አቅራቢ፤ ያሬድ ኃይለማርያም ሐምሌ 28 ቀን 2018 ብራስልስ፣ ቤልጂየም

ኢትዮጵያ ባለፉት 27 ዓመታት የሕግ የበላይነት በገፍ የተጣሰባት፣ ነጻ ዳኝነት እና ፍትህ የተጓደለባት፣ ሰብአዊ መብቶች እና የዜጎች መሰረታዊ ነጻነቶች ያለ ገደቢ የተጣሱባት፣ ማህበራዊ ፍትህ የተዛነፈባት እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የተዳፈነባት አገር ነበረች። በየጊዜው ብልጭ ብለው የተዳፈኑ ተስፋ ሰጪ የሆኑ እድሎች በአግባቡ ሳንጠቀምባቸው አልፈዋል። ለዚህም በምርጫ 1987 ወቅት የታዩ ሕዝባዊ መነቃቃቶች እና ጠንካራ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፉክክር መጨረሻው እንዳይሆን ሆኖ ተጠናቀቀ እንጂ ከሚጠቀሱት የመከኑ እድሎች መካከል አንዱ ነው። ከዚህ ምርጫ ማግሥት ጀምሮ ግን በተከታታይ በመንግሥት የተወሰዱት እርምጃዎች የታዩትን የዲሞክራሲ ጭላንጭሎች ያዳፈነ እና ሥርዓቱም ከለዘብተኛ አንባገነንነት (semi authoritarian) ወደ ለየለት አንባገነንነት (authoritarian) የተሸጋገረበት ወቅት ነበር። ሕጎች፣ የፍትሕ አካላት፣ ሕግ አውጪው፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙሃን እና መከላከያ ሠራዊቱ ጭምር የአፈና መዋቅሩ አካል ሆነው ቆይተዋል።

ሙሉውን ለማንበብ – ለውጡ የሰነቃቸው ተስፋዎች ፣ የተወሰዱ በጎ እርምጃዎች እና ያንጃበቡ አደጋዎች