የዘርና የቋንቋ ሥርዓተ- መንግሥት አገር ያተራምሳል

ታፈሰ በለጠ

በአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ የክልል፣ የዘር፣ የጎሣ፣ የጎጥና የቋንቋ ሥነ መንግሥታዊ ቡድኖች አሉ፡፡ በዜግነት ላይ የተመሠረተና አገር-አቀፍ ቡድን ካልተጠናከረ አንድ ቡድን ብቻውን አገሪቱን ማስተዳደር አይችልም፡፡ ምንጊዜም አናሳ ሆኖ ነው የሚገኘው፡፡ ወያኔ ብቻውን ኢትዮጵያን ማስተዳደር ስላልቻለ የአማራን እንዲሁም የኦሮሞና የደቡብ «ብሔሮችን»አአጣምሮ በበላይነት ለሀያ ሰባት ዓመታት «ክርን አማስት»አእያለ ቆየ፡፡ አሁን ግን ከወያኔ በስተቀር ሌሎቹ ክርስትና እየተነሱ «..ዴፓ» አተሰኝተዋል፡፡ ወያኔ አሁንም ነጻአውጪ ግንባርና ጠመንጃ ያልፈታ ነው፡፡ የሥነ መንግሥት (የፖለቲካ) ተወዳዳሪ ቡድኖች በዘር፣ በጎሣ፣ በአካባቢ ስምና በሃይማኖት ከተሰየሙና ከተንቀሳቀሱ አባሎቻቸውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው የየራሳቸው ሰዎች ይሆናሉ፡፡ ሁሉም ሁለንተናዊ ራዕይ አይኖራቸውም፡፡ የአማራ ሥነ መንግሥት ቡድን አባልነት ካልተስማማኝ ወደ ኦሮሞው ለመቀላቀል እንዴት እችላለሁ፤ ኦሮሞ መሆን አለብኝ፡፡ መርሆዉና ዓላማው በራሱ አቀፍ መልካም ቢመስልም በአባልነት ተቀባይነት አይኖረኝም፡፡ የትግራይ የነጻነት ግንባር አባልም መሆን አልችልም፡፡ ከትግራይ ሰው በስተቀር የሌላ አካባቢ ሰው አባል ነው ሲባል አልሰማሁም፡፡

ይቀጥሉ